loading
የኢራን ፕሬዚዳንት አሜሪካ በምታደርገው ምርጫ ሀገራቸው መደራደሪያ ሆና አትቀርብም አሉ ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 የኢራን ፕሬዚዳንት አሜሪካ በምታደርገው ምርጫ ሀገራቸው መደራደሪያ ሆና አትቀርብም አሉ ፡፡የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ በቨርቹዋል በተካሄደው 75ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኢራን በአሜሪካ ምርጫም ሆነ በውስጥ ጉዳይ ላይ በጭራሽ መደራደሪያ ሆና አትቀርብም ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው የሀገራችን ክብርና ብልጽግና ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊያችን ነው ያሉ ሲሆን […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶች በ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶች በ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የጀመረችው የ”ገበታ ለሀገር” መርሃ ግብር የሸገር ፕሮጀክት ተከታይ ምዕራፍ ነው። በኢትዮጵያ ጎርጎራ፣ ኮይሻና ወንጪ የሚገነቡት “የገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።በመሆኑን ዓለም […]

በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ:: በሀገሪቱ በምንግስት ወታደሮች እና ነፍጥ አንግበው ጥቃት በሚያደርሱ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በርካታ ዜጎችን የእንግልትና የስቃይ ሰለባ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ በተባለው አካባቢ ታጣቂዎቹ የሚያደርሱት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህም […]

በአዲስ አበባ የሚገኙ 26 የግል የትምህርት ተቋማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለባቸው የኢኮኖሚ ጫና የሙያ ፈቃዳቸውን መለሱ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 በአዲስ አበባ የሚገኙ 26 የግል የትምህርት ተቋማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለባቸው የኢኮኖሚ ጫና የሙያ ፈቃዳቸውን መለሱ።የከተማ አስተዳደሩ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን እንዳስታወቀዉ  ከእነዚህ መካከል 11 መዋዕለ ህጻናት፤ 13 የአንደኛ ደረጃና ሁለቱ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸዉ፡፡ 670 የግል የትምህርት ተቋማት ደግሞ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማግኘታቸውም ተገለጿል።የባለስልጣኑ […]

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል:: ማሊ ማእቀቡ የተጣለባት ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ነው፡፡ መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር በበላይነት የመራው ኢኩዋስ ማእቀቡ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ለዓርብ […]

ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች:: በዓሳ ሀብት ልማት ተቋም ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ግለሰብ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ደብዛቸው ጠፍቶ እንደነበር የገለፀችው ሴኡል በመጨረሻ በሰሜን ኮሪያ የባህር ጠረፍ አስከሬናቸው መገኘቱን አረጋግጣለች፡፡ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ሰውየውን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተኩሰው ገድለው ሲያበቁ በጭካኔ አስከሬናቸው […]

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ:: ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ2013 በጀት ዓመት ለማከናወን ባቀዳቸው ተግባራትና በአስር አመት መሪ እቅዱ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። በመድረኩም የህግ አወጣጥና አተገባበር፣ የሰብአዊ መብትና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። በጠቅላይ አቃቤ ህግ […]

የምስራቅ ሐረርጌ አገረ ስብከት የመስቀል በዓል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚያከብር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የምስራቅ ሐረርጌ አገረ ስብከት የመስቀል በዓል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚያከብር አስታወቀ:: በሐረሪ ክልል የደመራና የመስቀል በዓልን ሐይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአንድነትና እርስ በርስ በመደጋገፍ በጥንቃቄ እንደሚከበር ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት የገለፀው። የምስቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት የትምህርትና ስልጠና ክፍል ሃላፊ መልዓከ […]

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች። በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው።የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል።

የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ:: የፓርቲው መሪ የቀድሞው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልመሃዲ እስራኤል ከአረቡ ዓለም ጋር የጀመረችውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት መደገፍ እጅ እንደመስጠት ይቆጠራል ብለዋል፡፡ ኖርማላይዜሽን በሚል አዲስ ታክቲክ እስራኤል የጀመረችው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ መስፈፀሚያ ነው ሲሉም […]