loading
ናይጄሪያዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት ጫፍ ላይ ደርሰዋል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 ናይጄሪያዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት ጫፍ ላይ ደርሰዋል:: የቀድሞዋ የናይጄሪያ የገንዘብ ሚንስትር ንጎዚ ኦኮንጆ ከደቡብ ኮሪያዋ ተፎካከሪያቸው ጋር የመጨረሻውን ዙር ውድድር ተቀላቅለዋል፡፡ የሃርቫርድ ዩንቨርሲቲ ምሩቅ የሆኑት ኦኮንጆ እና የመጨረሻው ዙር የደረሱት የኬንያ፣ የሳኡዲ አረቢያ እና የእንግሊዝ ተወዳዳሪዎችን በልጠው በመገኘታቸው ነው፡፡ ሀገራቸውን ደቡብ ኮሪያን በገንዘብ ሚኒስትርነት እያለገሉ የሚገኙት ዩ ሚዩንግ […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህመማቸው አገግመው በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይመለሳሉ ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህመማቸው አገግመው በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይመለሳሉ ተባለ:: በቤተ መንግስታቸው ተወሽበው የከረሙት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን ሀኪሞቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያ በዋይት ሀውስ ቀጥሎም በወታደራዊ ሆስፒታል ህክምናቸውን የተከታተሉት ትራምፕ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ጊዜየን ማጥፋት አልፈልግም የምጫ ክርክሬን በፊት ለፊት ማድረግ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ […]

13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ::13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሃገራዊ ብልጽግናችን!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡የሰንደቅ ዓላማ ቀኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ አርበኞች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው የተከበረዉ፡፡ ቀኑ በየዓመቱ የተለያየ መሪ ቃል እየተቀረፀለት በፌደራል፣ በክልልና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በዋናነት ስለሰንደቅ […]

ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረጉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ እንቅስቃሴን ጎበብኝተዋል መሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው የሚያካሂዳቸውን የምርምርና የግንባታ እንቅስቃሴዎች መጎብኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ስኬታማ የሆነ […]

በኢትዮጵያ ከ100 ሺህ ሰዎች አምስት ሰዎች በወባ በሽታ ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 በኢትዮጵያ ከ100 ሺህ ሰዎች አምስት ሰዎች በወባ በሽታ ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ተገለጸ::የወባ በሽታ ስርጭት ተመልሶ ማንሰራራቱን የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡ባለፉት ሁለት ዓመታት የወባ በሽታ ስርጭት ተመልሶ እየተንሰራራ መምጣቱን የገለጸዉ ሚኒስቴሩ ፤በሽታውን ለመከላከል አመራሩ፣ ህብረተሰቡና የጤና ባለሙያው በትኩረት እንዲሰሩም ተጠቁሟል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ድጉማ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት […]

በከተማ ልማት ዕቅድ ላይ የሚመክረው ጉባኤ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ይጀምራል::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 በከተማ ልማት ዕቅድ ላይ የሚመክረው ጉባኤ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ይጀምራል::”የብልፅግና ማዕከላት ከተሞች እና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን እንዱስትሪን ለመገንባት በጋራ እንሰራልን”!! በሚል መሪ ሀሳብ ከጥቅምት 05 -07 2013 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር የቀጣይ 10 ዓመታት መሪ ዕቅድ ትግበራ ማስጀመሪያ ጉባኤ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ የጉባኤው ዋና […]

በአንድ ወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጡ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 በአንድ ወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጡ:: ባሳለፍነው መስከረም ወር ብቻ ከ10 ሺህ በላይ የትራፊክ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎችን መቅጣቱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋከል፡፡ ኤጀንሲው በመስከረም ወር ብቻ የትራፊክ ህግ እና ደንብን ለማስከበር ባደረኩት የቁጥጥር 10 ሺህ 711 አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንብ ሲተላላፉ […]

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች ቅድሚያ ለሀገር ሰጥተው እንዲስማሙ ጠየቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች ቅድሚያ ለሀገር ሰጥተው እንዲስማሙ ጠየቀ:: ድርጅቱ በሁለት ጎራ ተከፍለው ጦርነት ውስጥ የገቡት ወገኖች ከራሳቸው ይልቅ ቅድሚያ ለሀገራቸውና ለህዝቡ በመስጠት እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ነው ያሳሰበው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተጠባባቂ ልዩ ልኡክ ስቴፋኒ ዊሊያምስ በድርድሩ ወቅት ከራስ የፖለቲካ አከንዳ ይልቅ የሀገሩን ጉዳይ የሚያስቀድም ተወያይ እንጠብቃለን […]

የጊኒ ተቃዋሚዎች መንግስት በአባሎቻቸው ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 የጊኒ ተቃዋሚዎች መንግስት በአባሎቻቸው ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ:: ጊኒ ከአምስት ቀናት በኋላ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ለሶስተኛ ጊዜ እወዳዳራለሁ በማለታቸው ምክንያት ከባድ ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ ሰነባብቷል፡፡ በሀገሪቱ የሚነቀሳቀሱት ተቃዋሚዎች እንደሚሉት መንግስት የተነሳበትን ተቃውሞ ለማስቆም በወሰደው የሃይል እርምጃ ከ90 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የጊኒ የደህንነት ሚኒስትር አልበርት ዳማንታንግ ካማራ ግን በተቃዋሚዎቹ […]

ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::የባንኩ ዳሬክተሮች ቦርድ ይፋ ባደረገው መሰረት ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢና ለዜጎቻቸው ምርመራና እንክብካቤ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጽድቋል የገንዘብ ድጋፉ ለአንድ ቢሊዮን ሰዎች ክትባት ማዳረስ የሚያስችል ሲሆን የዓለም ባንክ እስከ ፈረንጆቹ […]