በኢትዮጵያ ፍትህ እንዲረጋገጥ ብዙ ስራዎች ይቀራሉ-ኢ.ሰ.መ.ኮ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ለሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡ ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የ10 ወር የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕ እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡ ኮሚሽኑ ባለፉት 10 ወራት ግጭት የተከሰተባቸው 65 ቦታዎችን መድረሱን፣ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 450 ሺህ ስደተኞችን የሚያስጠልሉ አስር […]