loading
የዓለም አቀፍ ምሁራን ግልፅ ደብዳቤ ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ

በመላው ዓለም ከፍተኛ ተደማጭነትና ተፅዕኖ ያላቸውና አሜሪካና ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ምሁራን እና የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች፣ በትግራይ ክልል በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካላት ሲፈፀሙ የታዘቧቸውን ሚዛናዊነት የሌላቸው ተግባራት በግልፅ በመናገራቸው፤ በድርጅቱ የሥራ ዕገዳ የተጣለባቸው ሁለት የመንግሥታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪዎች አስፈላጊ ከለላ እንዲደረግላቸውና ወደሥራቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ግልፅ ዓለም አቀፋዊ ደብዳቤ […]

ሐሰት፡ ይህ ምስል በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም።

ምስሉ የተወሰደው አዶቤ ስቶክ ከተሰኘ የምስል መገበያያ ድረ-ገጽ ላይ ነው። በልጥፉ ላይ “ደሴ ባለስልጣኖች ያረፉበት ሆቴል በጁንታው ተመታ” የሚለው ጽሁፍ ሐሰተኛ ነው። ይህ የፌስ ቡክ ልጥፍ “ደሴ ባለስልጣኖች ያረፉበት ሆቴል በጁንታው ተመታ ! የመከላከያ ጀነራል ሞተ።አሁን ከደሴ አሳዛኝ መረጃ” ይላል። የያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) እና የቲንአይ የምስል ፍለጋ (tineye image search) የጥምር ውጤት […]

ሐሰት፡ ይህ ምስል የህወሓት አማጽያን አንዋጋም ያሉትን ወጣቶች ሲረሽኑ አያሳይም።

ምስሉ የባንግላዲሽ ወታደሮች ከባድ ስልጠና ሲሰለጥኑ ያሳያል። ጁንታው (ህወሓት) አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ወጣቶችን ረሸናቸው በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ምስል ሐሰተኛ ነው። በልጥፉ ላይ በአማርኛ ቋንቋ የተጻፈው ጽሁፍ “ጁንታው አንዋጋም ያሉትን ወጣቶችን እረሸናቸው።እግዚኦ ! የትግራይ ወጣቶች አለቁ” ይላል፡፡ የያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) ውጤት እንደሚያሳየው ይህ ምስል እ.ኤ.አ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ከተለቀቀው የዩትዩብ ቪዲዮ ልባስ […]

ሐሰት: የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው ፌዴራል መንግሥት ጫና ያደርግብናል አላሉም።

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው ከወላይታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄም ጋር ተያይዞ የፌዴራል መንግሥት ጫና ማድረጉን የሚገልጽ መግለጫ አልሰጡም። የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው “የወላይታ ጥያቄ እጅግ በጣም እያሳሰበኝ ነው” ብለዋል የሚለው የፌስቡክ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው። በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ  “#ሰበር #ዜና #የደቡብ #ክልል #ርዕስ #መስተዳድር #አቶ #ርዕስቱ #ስለ #ወላይታ #እውነታውን #ተናገሩ “ሆኖም የወላይታ ጥያቄ […]

የተጭበረበረ ፡ ይህ ምስል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወታደሮች ተይዘው አያሳይም።

ትክክለኛው ምስል የህወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ሲገቡ ያሳያል። ልጥፉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በለበሱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ አስመስሎ ለማቅረብ ሞክሯል። ልጥፉ “ዛሬ የደረሰን ሰበር መረጃ ሽመልስ አብዲሳ ታሰረ” ይላል። የጎግል የምስል ፍለጋ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው የልጥፉ […]

ሐሰት: ይህ ምስል MI-35 የተሰኘ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ ተመቶ አያሳይም።

ምስሉ የተወሰደው ዘ ታይምስ ከተባለ በለንደን የሚገኝ የብሪቲሽ ዕለታዊ ብሔራዊ የጋዜጣ ድህረገስፅ ላይ ነው። ምስሉ የኢራቅ የጦር ሄሊኮፕተር በሰሜን ኢራቅ በሞሱል አቅራቢያ የሚገኙ የአይሲስ ቦታዎችን ሲደበድብ ያሳያል። ይህ የፌስቡክ ልጥፍ “#ሰበር #ዜና #ትግራይ #ትስዕር የትግራይ ሰራዊት አየር ሀይል ምድብ MI-35 የተሰኘ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ መቶ መጣሉን የትግራይ ሰራዊት ሰንተራል ኮማንድ ቃላቀባይ ጌታቸው ረዳ […]

ሐሰት: ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው አላሉም።

ምስሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የ2014 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ነው።  በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ  “#ሰበር #ዜና ለመጀመሪያ ጊዜ የኢፌዴሪ  ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ እውነት ተናገሩ  ይሄ ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው በማለት ለፈረንሳይ መጽሔት ገልፃለች” ይላል። እ.ኤ.አ ህዳር 22-2021  War in Ethiopia: the disarray of President Sahle-Work […]

ሐሰት: ይህ ምስል የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ በድሮን መመታቱን አያሳይም።

የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ምንም አይነት በከባድ የጦር መሳርያ የደረሰ ጉዳት የለም። በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ “#ሰበር #ዜና የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በድሮን ተመታ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው ቡድን የተከዜ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተገለፀ። የህውሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸዉ ረዳ በቲዊተር ገፃቸዉ እንደገለፁት ከሆነ ዛሬ ጣዋት አከባቢ ጥቃቱ በግድቡ […]