አውሮፓ ህብረት ከቻይና እና አሜሪካ ጋር በአፍሪካ የሚያፎካከረውን አዲስ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ::
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ያለውን ግንኙነት በእጥፍ እንደሚጨምር የተነገረለትን አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ነው ይፋ ያደረገው፡፡ ህብረቱ ይፋ ያደረገው አዲስ ስትራቴጂ በአፍሪካ ንግድ እና ኢንቨስትመንት የቻይና ፣የአሜሪካንና የሩሲያን ድርሻ ለመጋራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አውሮፓ ከአፍሪካ ጋር ያለው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 235 ቢሊየን ዩሮ ቢደርስም በቻይናና በአሜሪካ […]