SportSports

በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ከሲቪያ ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ

በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ከሲቪያ ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ

የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ የሩብ ፍፃሜ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ግጥሚያዎች ከትናንት ጀምሮ እየተከናወኑ ሲሆን ዛሬ ምሽትም አንድ ጨዋታ ይደረጋል፡፡

ትናንት ምሽት ሄታፌ በሜዳው ተጫውቶ ቫሌንሲያን በሞሊና ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ዛሬ ምሽት 4፡30 ላይ ደግሞ ሲቪያ በራሞን ሳንቼዝ ፒዡዋን ስታዲየም ባርሴሎናን ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው የውድድር ዓመት የንጉስ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚ የነበሩ ሲሆን ባርሳ 5 ለ 0 ድል በማድረግ ዋንጫውን ወደ ካታላን ካዝና ቀላቅሎታል፡፡ በዚህ ወር መጀመሪያ በላሊጋው ተገናኝተው በካምፕኑ እንዲሁ ባርሴሎና የ4 ለ 2 ውጤት በአንዳሉዥያው ቡድን ላይ አስመዝግቧል፡፡

በምሽቱ ግጥሚያ አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ የቡድኑን አምበል ሊዮኔል ሜሲ የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ሊያካትቱት እንደሚችል ተነግሯል፤ ኦስማን ዴምቤሌ፣ ጄሰን ሙሪዮ፣ ሳሙኤል ኡምቲቲ እና ቶማስ ቨርማለን በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ ናቸው፡፡

በሲቪያ በኩል የክንፍ መስመር ተሰላፊው ኖሊቶ እና አማካዩ ማክሲም ጎናሎንስ በጉዳት ግልጋሎት አይሰጡም ተብሏል፡፡

በግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታዎች በነገው ዕለት ሲከናወኑ፤ ካታላን ላይ ኢስፓኞል ሪያል ቤቲስን እንዲሁም ሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ ቤርናባው ጅሮናን ያስተናግዳሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button