loading
በማዳጋስካር ምርጫ አንድሪ ራጆሊና ድል ቀንቷቸዋል

በማዳጋስካር ምርጫ አንድሪ ራጆሊና ድል ቀንቷቸዋል አሸናፊና ተሸናፊዎቹ ፕሬዝዳንቶች እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2009 በሚገባ ይተዋወቃሉ፡፡ የአሁኑን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፍ ያቃታቸው ማርክ ራቫሎማናና ማዳጋስካርን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ በነበረበት ወቅት የአሁኑ ባለድል አንድሪ ራጆሊና ደግሞ የአንታናናሪቮ ከንቲባ ነበሩ፡፡ የኋላ ኋላ ግን ራጆሊና ከመከላከያ ሀይሉ ጋር በማበር ራቫሎማናና ከስልጠን እንዲወርዱ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል ነው የሚባለው ፡፡ ከዚያም ራጆሊና በፈረንጆቹ […]

አልበሽር ወታደሮቻቸውን በመልካም ቃላት እያባበሉ ነው

አልበሽር ወታደሮቻቸውን በመልካም ቃላት እያባበሉ ነው የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር  በአትባራ አቅራቢያ በሚገኘው ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ጦር ሰራዊታችን ይህን መንግስት በሀይል ለመጣል ከሚያሴሩት ጋር ባለማበሩ ላቅ ያለ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልሽር በ30 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው እንደ ዘንድሮው ያለ ተቃውሞ ደርሶባቸው አያውቅም፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ከተቃውሞ ሰልፈኞች በኩል […]

የካቶሊክ  ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው

የካቶሊክ  ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው፡፡ የኮንጎን የምርጫ ሂደት ከታዘቡት ተቋማት መካከል በሀገሪቱ ትልቅ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ የምርጫው ውጤት ሲገለፅ አሸናፊው እና እርሷ የታዘበቸው እውነታ እንዳልተገጣጠመላት በይፋ ተናግራለች፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የአፍሪካ ህብረት እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ታዛቢዎችም የቤተ ክርስቲያኗን ሀሳብ ይጋራሉ፡፡ ነገር ግን […]