loading
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው የማዕከላዊ አፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሜሪ ኖኤል ኮዬራ ሩሲያ በሀገራችን  የጦር ሰፈር ለመገንባት ያቀረበችውን ጥያቄ በመልካም ጎኑ ነው የምናየው ብለዋል፡፡ ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ሩሲያ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለማሰልጠን ሙያተኞቿን ስትልክ በመርህ ደረጃ በሀገሪቱ የጦር ሰፈር ለመገንባት የሚያስችላትን ስምምነት አድርጋለች ፡፡ እስካሁን ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ባንወያይም ወደፊት የሁለቱም […]

ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሸንፏል

ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሸንፏል የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመቀላቀል የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ ትናንት የሞሮኮውን ሃሳኒያ ዩኒዬን ስፖርት አጋዲር በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ጅማ አባ ጅፋር የ 1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሙሉ ጨዋታው በጣት ከሚቆጠሩ የግብ ሙከራዎች ውጭ ያን ያህል ሳቢ ያልነበረ፤ በሁለቱ ቡድኖች ያን ያህልም ኢላማውን […]

በካርቱም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አልደገፉም የተባሉ አንድ የሃይማኖት አባት ከመስጊድ ተባረሩ

በካርቱም አንድ የሀይማኖት አባት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ባለመደገፋቸው ህዝቡ ከመስጊድ አባርሯቸዋል ተባለ ። ሱዳን ውስጥ ካሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ የሆኑት ኢማም አብዱል ሀይ ዩሱፍ  ተቃውሟውን  እየመሩ አይደለም በሚል ከአማኞች በቀረበባቸው  ውንጀላ  ነው ከመስጊድ  የተባረሩት። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ መንግሥትን በመደገፍ የሚታወቁትን  እኚህን ኢማም አንድ ግለሰብ ሲቆጣቸው ታይቷል። ሮይተርስ እንደዘገበው ባለፈው አርብ […]

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የድምፅ ቆጠራ ውጤት ይፋ ቢደረግም፤ በተፎካካሪዎች ዘንድ የተሳሳተ ነው መባሉን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ)  የድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታከናውን ጥሪ አቅርቦላታል፡፡ ኮንጎ ነፃነቷን ከተቀዳጀች ከ59 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ማብሰሪያ  ይሆናል ብሎ ተስፋ የተጣበት ምርጫ […]

ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው

ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው፡፡ የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የፑቲንን ድጋፍ ፍለጋ ባለስልጣኖቻቸውን አስከትለው ሞስኮ ገብተዋል፡፡ በሀገር ቤት በዋጋ ንረት ሳቢያ  የተቃውሞ ሰልፍ ረፍት የነሳቸው ምናጋግዋ ክሬምሊን ከገቡ በኋላ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ሀገሬ ከኢኮኖሚ ችግር ትላቀቅ ዘንድ እንደታላቅ ወንድም አቅፈው ደግፈው እንዲያግዙኝ አፈልጋለሁ ብለዋቸዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሩሲያን ጨምሮ […]

የሊቢያ ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን አፈረሱ።

የሊቢያ ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን አፈረሱ በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በተቀናቃኝ ሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት አምስት ሰዎች ሲገደሉ 20 የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡ ሬውተርስ የሀገሪቱን የጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው በተፋላሚ ሀይሎቹ መካከል ከአራት ወራት በፊት የተፈረመው  ተኩስ አቁም በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም አስገኝቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት 7ኛው ብርጌድ ወይም ካኒያት ተብለው በሚጠሩት እና ትሪፖሊ ፕሮቴክሽን […]