loading
የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በሱዳን እና በሊቢያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ካይሮ  ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡ ህብረቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ ምክር ቤቱ በ15 ቀናት ውስጥ ስልጣኑን ለሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲያስረክብ ይህ ባይሆን ግን ሱዳን ከህብረቱ እንደምትባረር አስጠንቅቆ ነበር፡፡ የግብፁ የዜና ወኪል ሜና […]

ሱዳናዊያን በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት ይበጃቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ

ሱዳናዊያን በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ውይይት መፍታት ይበጃቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ ምክተል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከረ ባለው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ውይይት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው የሱዳን ፖለቲከኞችና ባለድርሻ አካላት በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ […]

አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ

አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ። ባለቤትነቱ የኤር ዚምባብዌ  የሆነ ቦይንግ-ሰራሽ የቦይንግ 767-200ኤር አውሮፕላን ነው ሞተሩ በሚገኝበት የአውሮፕላኑ ጅራት ላይ  እሳት የፈጠረው፡፡ ይህ አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ  ከተነሳ በኋላ  ነው ብልሽቱ እና የእሳት ብልጭታው የታየው ሲል የሃገሪቱ አየር መንገድ ያስታወቀው፡፡ በብልሽቱ በረራው አለመስተጓጉሉና አውሮፕላኑ ሀራሬ በሰላም ደርሶ ማረፉን ኤር ዚምባብዌ ገልጿል፡፡ የዙምባቡዌ አየር መንገድ የብልሽቱን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል፡