loading
በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ:: በሀገሪቱ በምንግስት ወታደሮች እና ነፍጥ አንግበው ጥቃት በሚያደርሱ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በርካታ ዜጎችን የእንግልትና የስቃይ ሰለባ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ በተባለው አካባቢ ታጣቂዎቹ የሚያደርሱት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህም […]

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል:: ማሊ ማእቀቡ የተጣለባት ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ነው፡፡ መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር በበላይነት የመራው ኢኩዋስ ማእቀቡ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ለዓርብ […]

የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ:: የፓርቲው መሪ የቀድሞው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልመሃዲ እስራኤል ከአረቡ ዓለም ጋር የጀመረችውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት መደገፍ እጅ እንደመስጠት ይቆጠራል ብለዋል፡፡ ኖርማላይዜሽን በሚል አዲስ ታክቲክ እስራኤል የጀመረችው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ መስፈፀሚያ ነው ሲሉም […]

የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ:: የሽግግር ወቅቱ ፕሬዚዳንቱ ባህ ንዳዉ የሀገሪቱ ጠቅላይሚኒስትር አድርገው የሾሙት የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞክታር ኡኔን ነው፡፡ የማሊ የሽግግር መንግስት ሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ከምእራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማላላት ሁነኛ መንገድ ሊሆንለት ይችላል ተብሏል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የማሊ ጄኔራሎች ፕሬዚዳንት ቡበከር […]

በማሊ የወባ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ በርካቶችን ለሞት መዳረጉ ተነገረ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 በማሊ የወባ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ በርካቶችን ለሞት መዳረጉ ተነገረ::በሰሜናዊ ማሊ ግዛት የወባ ወረርሽኝ መቀስቀሱንና በአንድ ሳምንት ውስጥ 23 ሰዎች መሞታቸውን የጤና ባለሙያዎች ይፋ አድርገዋል የማሊ ጤና ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል 59 ሰዎች በወረርሽኙ ምክኒያት መሞታቸውን አስታውቋልይህም የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር […]

የአልበሽር ጠበቆች ቅሬታ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2013 የአልበሽር ጠበቆች ቅሬታ::በአቃቤ ህግ ቅር የተሰኙ የአልበሽር ጠበቆች ችሎት ረግጠው ወጡ:: የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ተከላካይ ጠበቆች አቃቤ ህግ አድሏዊ የሆነ ክርክር አቅርቦብናል ሲሉ ከሰዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከፕሬዚዳንቱ ጠበቆች መካከል የተወሰኑት የዕለቱን ክርክር በመተው ችሎቱን ረግጠው መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አልበሽር በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እስከሞት […]

ናይጄሪያዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት ጫፍ ላይ ደርሰዋል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 ናይጄሪያዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት ጫፍ ላይ ደርሰዋል:: የቀድሞዋ የናይጄሪያ የገንዘብ ሚንስትር ንጎዚ ኦኮንጆ ከደቡብ ኮሪያዋ ተፎካከሪያቸው ጋር የመጨረሻውን ዙር ውድድር ተቀላቅለዋል፡፡ የሃርቫርድ ዩንቨርሲቲ ምሩቅ የሆኑት ኦኮንጆ እና የመጨረሻው ዙር የደረሱት የኬንያ፣ የሳኡዲ አረቢያ እና የእንግሊዝ ተወዳዳሪዎችን በልጠው በመገኘታቸው ነው፡፡ ሀገራቸውን ደቡብ ኮሪያን በገንዘብ ሚኒስትርነት እያለገሉ የሚገኙት ዩ ሚዩንግ […]

የጊኒ ተቃዋሚዎች መንግስት በአባሎቻቸው ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 የጊኒ ተቃዋሚዎች መንግስት በአባሎቻቸው ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ:: ጊኒ ከአምስት ቀናት በኋላ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ለሶስተኛ ጊዜ እወዳዳራለሁ በማለታቸው ምክንያት ከባድ ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ ሰነባብቷል፡፡ በሀገሪቱ የሚነቀሳቀሱት ተቃዋሚዎች እንደሚሉት መንግስት የተነሳበትን ተቃውሞ ለማስቆም በወሰደው የሃይል እርምጃ ከ90 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የጊኒ የደህንነት ሚኒስትር አልበርት ዳማንታንግ ካማራ ግን በተቃዋሚዎቹ […]

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የከሰላውን አስተዳዳሪ ከስልጣናቸው አነሱ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የከሰላውን አስተዳዳሪ ከስልጣናቸው አነሱ:: ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ባለፈው ሰኔ ወር የከሰላ ግዛት አስተዳዳሪ አድርገው ሾሟቸውን ሳልህ አማርን ከስልጣናቸው ያወረዷቸው በአካባቢው ከተነሳው የጎሳ ግጭት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው  ተብሏል፡፡ አማር ለግዛቲቱ የመጀመሪያው የሲቪል አስተዳዳሪ ሆነው ከተሸሙ ጀምሮ ቤጃ ከተባሉት ጎሳዎች ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን ወደ ግዛቲቱ እንዳይገቡ […]

ዩጋንዳውዊ አርቲስት እና ፖለቲከኛ ሮበርት ኪያጉላኒ ዳግም እስር ቤት ገባ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 ዩጋንዳውዊ አርቲስት እና ፖለቲከኛ ሮበርት ኪያጉላኒ ዳግም እስር ቤት ገባ::በቅፅል ስሙ ቦቢ ዋይን እየተባለ የሚጠራው ዩጋንዳዊው የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝና ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ከአሁን በፊትም መንግስትን ተቸህ ተብሎ በተደጋጋሚ ለእስርተዳርጎ ያውቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒን አጥብቆ በመተቸት የሚታወቀው ቦቢ ዋይን አዲስ ባቋቋመው ፓርቲ ፅህፈት ቤቱ በፖሊስ ተይዞ መወሰዱን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡ ጠበቃው አክለው እንዳሉት […]