loading
ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 31 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ 94 በመቶ በሆነ ድምፅ አሸንፈዋል መባሉን ተከትሎ ከረር ያለ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፡፡ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር የህገ መንግስ ማሻሻያ ሲያደርጉ ጀምሮ ነበር በሀገሪቱ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ኦታራ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሏቸውን ተቃዋሚዎች […]

ኢጋድ በሬይክ ማቻር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እገዳ አነሳ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 ኢጋድ በሬይክ ማቻር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እገዳ አነሳ:: የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በተቀናቃኝ መሪው ሬይክ ማቻር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እገዳ ሙሉ በሙሉ አነሳ፡፡ እገዳው የተነሳው ጦርነቱ ቆሞ ተቀናቃኝ አካላቱ ከስምምነት ላይ ደርሰው በጋራ መስራት በመጀመራቸው ነው፡፡ በዚህም ማቻር የቀጣናዊው ተቋም  አባል ወደሆኑ […]

በጋራ የድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለዉጦችን የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ በመሆናቸዉ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢትዮጵያ አሳሰበች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 በጋራ የድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለዉጦችን የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ በመሆናቸዉ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢትዮጵያ አሳሰበች:: የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሰክሬተርያት ጽ/ቤት ለአርትስ በላከዉ መረጃ እንዳስታወቀዉ፤ ሱዳን ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ ድንበር አካባቢ የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ ፤እና መሬት ላይ ያለዉን እዉነታ የሚለዉጡ እንቅስቃሴዎችን እያደረገች እንደሆነና እንቅስቃሴዉ በአስቸኳይ እንደቆምና ወደቀደመዉ ቦታ እንዲመለስ የኢትዮጵያ […]

በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ከ75 ዓመት በኋላ ውቅና አገኙ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ከ75 ዓመት በኋላ ውቅና አገኙ:: ወደ 80,000 የሚሆኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያን እንደ የወታደራዊ ጓድ አካል ሆነው በጦርነቱ ቢሳተፉም ከነጭ ወታደሮች ያነሱ ተደርገው የእነሱ አስተዋፅዖ ሳይነገር ተዳፍኖ ቀርቶ ነበር፡፡ አሁን ግን በኮመንዌልዝ በኩል በተቋቋመው ኮሚሽን በወቅቱ ለተዋጉትና ለሞቱት እንዲሁም አሁንም በህይዎት ለሚገኙ ወታደሮች የመታሰቢያ ሂደት […]

በማዕከላዊ አፍሪካ ምርጫ በተከሰተ ብጥብጥ 800 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በማዕከላዊ አፍሪካ ምርጫ በተከሰተ ብጥብጥ 800 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ የምጫ ኮሚሽን አስታወቀ:: የታጠቁ ሃይሎች ምርጫው በኪካሄድበት ወቅት ባደረሱት ጥቃት 14 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያዎችን ለመዝጋት መገደዱን ነው ኮሚሽኑ የገለፀው፡፡ ታጣቂዎቹ በመራጮችና በምርጫ ሰራተኞች ላይ ጥቃት በመሰንዘር፣ እንዲሁም የምርጫ ኮሚሽኑ ስራውን እንዳያከናውን በማገድ ነው ሂደቱን ያደናቀፉት ተብሏል፡፡ የታጠቁ ሃይሎች በመራጮች ከማዋከብ […]

አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር የበሽታው ስርጭት በአፍሪካ አነስተኛ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ በ47 የአፍሪካ ሀገራት በበሽታው የተያዙባቸው ዜጎች ሳምንታዊ አማካይ ቁጥር 73 ሺህ መድረሱ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ አህጉር የበሽታውን የስርጭት መጠን […]

በኒጀር ፅንፈኛ ሃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 በኒጀር ፅንፈኛ ሃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ:: በሀገሪቱ መንግስት አክራሪ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ቡድኖቹ ጥቃቱን ያደረሱት በማሊ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ በሁለት መንደሮች ነው ተብሏል፡፡ የኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው መንደሮች በማቅናት የጎበኙ ሲሆን የተጎጂ ቤተሰቦችና ነዋሪዎቹን አበረታተዋል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ተዋጊ ሃይሎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ሁለት ተዋጊ ሚሊሻዎቻቸው […]

ኬንያ እና ሶማሊያ አሁንም በመልካም ጉርብትናቸው የሚቀጡሉበት መንገድ አልተዘጋም ተባለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 ኬንያ እና ሶማሊያ አሁንም በመልካም ጉርብትናቸው የሚቀጡሉበት መንገድ አልተዘጋም ተባለ:: ሶማሊያ ባለፈው ዲሴምበር ወር በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገባችብኝ በሚል መነሻ ከኬንያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን በይፋ አቋርጣለች፡፡ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸው ወደ ነበረበት እንዲመለስ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርጉ የአፍሪካ ህብረትም ውዝግቡ በሰላም እንዲፈታ አሳስቦ ነበር፡፡ ሶማሊያ ውስጥ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ኬንያዊያን ሰራተኞች እንዳሉና በኬንያም […]

ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች:: ደቡብ አፍሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ስላሳሰባት ነው፡፡ ድንበሮቹ ዝግ ሆነው በሚቆይበት ወቅትም ወደ ሀገሪቱ የሚገቡም ሆኑ ወደ ውጭ የሚወጡ ተጓዦች አይኖሩም ነው የተባለው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ለ20 ሚሊዮን ሰዎች […]

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ:: በዮቤ ግዛት በምትገኝ አንዲት መንደር አቅርቢያ በሚጓዙ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ላይ በድንገት በተከፈተ ጥቃት ነው ወታደሮቹ የተገደሉት ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የደፈጣ ተዋጊዎቹ በከባድ መሳሪያዎችና በሮኬት በሚወነጨፉ የእጅ ቦንቦች ጭምር ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡ ወታደሮቹ ጥቃቱ ከተፈፀመበት 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ […]