loading
የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡በመፈንቅለ መንግስት የመሪነቱን ስፍራ የያዙት አል ቡርሃን ጦሩ ከፖለቲካዊ ውይይቶች ራሱን እንደሚያግል ያስታወቁ ሲሆን የሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ እንደሚፈቅድ ገልፀዋል። የጄኔራሉ መግለጫ የተሰማው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁ መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መቀጠላቸውን ተከትሎ […]

ኢጋድ ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ችግር በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት መወሰኗን አደነቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 ኢጋድ ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ችግር በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት መወሰኗን አደነቀ፡፡39ኛው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነት፣ ኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ አካባቢያዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ለውጦች፣ እንዲሁም በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ዙሪያ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ መክሯል። የአባል ሀገራቱ መሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነትና በሰሜኑ […]

በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በተነሳ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በተነሳ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡ በግብፅ ዋና ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ 10 ህጻናትን ጨምሮ 41 ምእመናን ህይወታቸው ማለፉን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በአደጋው ህይወት ለማዳን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ፖሊሶችን ጨምሮ 45 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ጥቂቶቹ ከሆስፒታል መውጣታቸውን የሀገሪቱ ጤና […]