loading
የአፍሪካና የቻይና ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

ሮይተርስ እንዘገበው በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን እስካለፈው ዓመት ድረስ 170 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል፡፡ በመጭው መስከረም ወር ላይ  የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም  ቻይና ውስጥ ይካዳል፡፡ ፎረሙም በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት ለአቅም ግንባታ የሚውል 10 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ መድባለች፡፡ ገንዘቡ […]

ምናንጋግዋ ሀገሬን በ2030 ከድህነት አላቅቃታለሁ አሉ፡፡

የዚምባቡየው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አወዛጋቢውን የምርጫ ውጤት በአሸናፊነት አጠቃለውታል፡፡ አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ምናንጋግዋ ከ37 ዓመት ወዲህ የሀገሪቱ የመጀመሪያው በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡ መሪ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡ ምርጨውን አጭበርብረዋል ተብለው በተፎካካሪያቸው ወቀሳ የደረሰባቸው ፕሬዝዳንቱ አሁን በጋራ ሀገራችንን የምናሳድግበት ወቅት ስለሆነ አንድነታችንን እናጠናክር የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ምናንጋግዋ በሚቀጥሉት 11 ዓመታት ውስጥ ከድህነት የተላቀቀች፣ ህዘወቦቿ መካከለኛ […]

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአዲሱ ክትባት ሁለት ሰዎች ከኢቦላ ቫይረስ ነጻ ሆነዋል::

  በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ክትባት ውጤት እያሳየ መምጣቱን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አታውቋል፡፡ በቫይረሱ ተይዘው የሙከራ ክትባቱን ሲወስዱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ከበሽታው ነጻ ሆነው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ መደረጉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው ሁለቱ ሰዎች በተሰጣቸው ህክምና መዳናቸውን ተከትሎ ዓለማችን […]

የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያ ንቅናቄ በአስመራ ከተማ በተለያዩ ጉዳዮች መወያታቸው ተገለፀ።

ፋና እነደዘገበው የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው፥ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አደም መሀመድ የሚመራው የመንግስት ልዑክና በትህዴን ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ የሚመራ ልዑክ በአስመራ መወያየታቸውን አስታውቀዋል። አርትስ 23/12/2010