loading
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ቁጥር ወደ 30 ለማድረስ እየሰራሁ ነው አለ፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቁጥር ስድስት ደርሷል፡፡ የፓርኮቹ መገንባት እና ስራ ላይ መዋል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ውጤታማ እንደሚያደርግ እና አሁን ካሉት ስድስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደስራ የገቡ እና በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ መኖራቸውን በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረ እየሱስ ተናግረዋል፡፡ የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጥቅምት 2011 ስራ የሚጀምር ሲሆን በቂሊንጦም የመድሃኒት ማምረቻ ኢንዱስተሪ ፓርክ ሊገነባ መሆኑን ሰምተናል፡፡ […]

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በ2010 በጀት አመት 3.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘው አለ፡፡

ይህን ያለው ኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ ዛሬ ባቀረበው የአመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው፡፡ የተገኘው ገቢ ባለፈው አመት ከተገኘው የሚያንስ መሆኑን እና የባለፈው አመት ገቢ 4.1 ቢሊዮን እንደነበረ የኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በላቸው መኩሪያ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ በበጀተ አመቱ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም 3.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው ገቢ ያረገው የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ፣የመድሃኒት […]

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ::

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሰራተኞቹ ለኢቢሲ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ […]