loading
የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጋር አብሮ እንዲውለበለብ የሚደነግገው አዋጅ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመራ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ አመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ነዉ  የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ ከአገራችን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ጋር አብሮ እንዲውለበለብ የሚደነግገውን ረቂቅ አዋጅ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የመራው፡፡ምክር ቤቱ የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀንን በሚመለከት የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ […]

በመርካቶ ከ1ሺ በላይ ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ ቅጣት ተጣለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 ቅጣቱ የተጣለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሰባት ወራት በመርካቶ ባደረገው ቁጥጥር ነዉ፡፡ቅጣት የተጣለባቸዉ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን በአግባቡ ባልተጠቀሙና ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ በተገኙ አንድ ሺ 71 ግብር ከፋዮች ላይ ሲሆን፡ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዳደራዊ ቅጣት መጣሉን አስዉቋል። በቢሮው የህግ ተገዥነት ዘርፍ፤ የታክስ መረጃና የሽያጭ መመዝገቢያ አስተዳደር ዳይሬክተር […]

በሰሜን ጎንደር ደጋማ ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 በሰሜን ጎንደር ዞን ደጋማ ወረዳዎች ማለትም በየዳ፣ ጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች ባለፈ አድማሱን በማስፋት በወረዳዎች ስር በሚገኙ 32 ቀበሌዎች ላይ የአንበጣ መንጋው ተስፋፍቷል ተብሏል። የሰሜን ጎንደር ዞነ ግብርና መምሪያ የኤክስቴንሽን ቡድን መሪ አቶ ዋለ መርሻ ለአማራ ብዙሃን መገናኛ እንደገለጹት፡ መንጋው አሁን ላይ የሰብል ወቅት ባለመሆኑ ጉዳት ባያደርስም የመስኖ ሰብሎች ለይ ጥፋት […]

የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ላይ ይበልጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ላይ ይበልጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናገሩ፡፡ ይህንን ያሉት ከምክርቤቱ 14ተኛ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የጤና ሚኒስትርና  የህብረተሰቡ ጤና  እንስቲትዮት በሀገሪቱ ቫይረሱን በተመለከተ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በአብራሩበት ወቅት ነዉ ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየብስ በአየርም 520 ሺ የሚሆኑ መንገደኞች ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን 958ቱ […]

ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገር ሠላምና ዘላቂ ልማት መቆም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡

ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገር ሠላምና ዘላቂ ልማት መቆም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮነን በባህር ዳር “የጋራ ራዕይና ግብ ለአማራ ሕዝብ ዘለቄታዊ አንድነትና ሁለንተናዊ ስኬት” በሚል መሪ ሐሳብ  በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ አንደተናገሩት የታፈረች ሀገር መመሥረት የሚቻለው በትንንሽ አጀንዳዎች ላይ ጊዜን በማጥፋት ሳይሆን ትላልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት […]