loading
የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ:: የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ  ድጋፍ ያደረጉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡ድጋፉ በዋነኝነት ለኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ተግባር የሚውሉ ሲሆን 280 ካርቶን ወይም 1 ሺህ 700 ኪሎ ግራም የሆነ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ […]

ምክር ቤቱ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴ መራ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 ምክር ቤቱ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴ መራ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አደራሽ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ ውሳኔዎችን መርምሮ አጽድቋል።ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብን ተመልክቷል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ […]

ኢትዮጵያ ተ.መ.ድ ኮቪድ-19ን ለመግታት የጀመረውን ኢኒሺየቲቭ እንደምትደግፍ  ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 ኢትዮጵያ ተ.መ.ድ ኮቪድ-19ን ለመግታት የጀመረውን ኢኒሺየቲቭ እንደምትደግፍ  ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ:: የተባበሩት መንግስታት ባለአደራ ፈንድ ለኮቪድ 19 ምላሽ ለመስጠት የጀመረውን “Rise for All” ኢኒሺየቲቭ ኢትዮጵያ መቀላቀሏን ፕሬዚዳንቷ ትናንት አስታውቀዋል።በተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሃመድ ይፋ የሆነው ፕሮጀክት የዓለም ሴት መሪዎች ወረርሽኙ ያስከተለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመግታት የሚረዳ መፍትሄ ለማበጀት ህብረታቸውን፣ ጥረታቸውንና ሃብታቸውን በማቀናጀትና በማንቀሳቀስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በተጨማሪ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢርና ሶልበርግና የባርባዶስ አቻቸው ሚያ ሞትሊ የተ.መ.ድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሮች ፕሮጀክቱን ለመደገፍ  የሚያግዝ የቪዲዮ ውይይት አድርገዋል። “ኮቪድ19 ዓለም አቀፍ ቀውስ መሆኑን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት መዘግየት ሞትን መጥት ነው፤ ሁላችንም ተመሳሳይ ጠላትን የተጋፈጥን በመሆናችን ሰብዓዊ አቅማችንን አንድ ላይ በማስተባበር ለውጤት መሰለፍ አለብን” ብለዋል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ። “ቫይረሱን በተናጠል ወይም በአንድ አገር ጥረት ብቻ መግታት ስለማይቻል ተመድ ጋራ ትብብር ያቀረበውን ጥሪ እደግፋለሁ” ብለዋል።  የፈንዱ ግብ በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ሲሆን በሁለት አመታት ውስጥ ደግሞ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ያለመ ነው።በዚህም ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን አገሮች፣ ህፃናትን፣ ሴቶችንና ለአደጋ የተጋለጡ  የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ አቅጣጫ ተይዟል።

ሚኒስቴሩ በሃብት ማሰባሰብ ስትራቴጂ ካሰባሰበዉ ሀብት ዉስጥ 15 ሚሊዮን ብሩን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ተቋማት አስረከበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 ሚኒስቴሩ በሃብት ማሰባሰብ ስትራቴጂ ካሰባሰበዉ ሀብት ዉስጥ 15 ሚሊዮን ብሩን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ተቋማት አስረከበ፡፡የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ፤ ሚኒስቴሩ ባካሄደዉ የርክክብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ ባስተላለፉት መልዕክት ቫይረሱ በፍጥነት የሚዛመት በመሆኑ የቆየንበት  የመጠጋጋት፣ የመጨባበጥና የመሳሳም ልማድን መተዉ አለብን ብለዋል፡፡ ሚኒስትር ዲኤታዋ […]

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደረሰ:: በ24 ሰዓታት ውስጥ በ912 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ሁለት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 7 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል፡፡ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ በበሽታው ተይዘው እንክብካቤ ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል 66 […]

ጠቅላይ ሚስትር ዐብይ አህመድ ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 ጠቅላይ ሚስትር ዐብይ አህመድ ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ይህ ቀን የዓለም የዓለም ሠራተኞችን ሕይወት የቀየሩ የሠራተኞች ትግሎች የሚታወሱበት ቀን ነው ብለዋል፡፡ይህን ቀን በማሰብ ስለሰራተኛው ማኅበረሰብ ስንነጋገር ስለ ቀጣይዋ ኢትዮጵያ እየተነጋገርን እንደሆነ እናምናለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራችን ጉዞ አምራች ኢንዱስትሪውን ወደ ማስፋፋት እያመራ መሆኑን አውስተዋል፡፡በሠራተኛው […]

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ለሦስት ምሁራን የፕሮፌስርነት ማዕረግ ሰጠ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በማስተማርና ምርምር ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታዉቋል። የዩኒቨርስቲው ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እምሩ ለኢዜአ እንደተናገሩት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠው በተሰማሩባቸው የማስተማርና የምርምር መስኮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምሁራን ነው። የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠውም ለዶክተር ይሄነው ገብረስላሴ በአፈር ሳይንስ ፣ ለዶክተር አብርሃ ፀጋዬ በፕላንት ኢኮሎጂ ኤንድ ኢትዮ ቦታኒ እንዲሁም ለዶክተር ከፍያለው አለማየሁ በእንስሳት ብዜት የትምህርት ዘርፎች የላቀ ውጤት በማስመዘገባቸው እንደሆነ አብራርተዋል። ምሁራኑ በዩኒቨርስቲው በመማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን በማካሄድና ፅሁፎቻቸውን በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት በሚገኙ ጆርናሎች በማሳተም እውቅና ያተረፉ በመሆናቸው ነው ብለዋል ። ሙሁራኑ በተጨማሪም ተማሪዎችን በማማከር፣ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ተመድበው በሰጡት የአመራር ብቃትና ባስመዘገቡት ውጤት ተመዝነው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድተዋል ።የምሁራኑን አስተዋጽኦ የዩኒቨርስቲው ሴኔት ገምግሞ ያቀረበውን ውጤት በስራ አመራር ቦርድ በማፀደቅ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው ከዶክተር ዘውዱ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

አዋጁን የተላለፉ አሽከርካሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 በወላይታ ዞን የአዋጁን ድንጋጌ ተላልፈዋል የተባሉ 700 አሽከርካሪዎች ተቀጡበወላይታ ዞን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክልከላ ድንጋጌን ተላልፈው ተገኝተዋል የተባሉ 700 አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን የዞኑ የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል ገለጿል፡፡በሌላ በኩል በሃዲያ ዞን የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ኮሮናን ለመከላከል የሚረዱ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎችን በፈጠራ ስራ በማውጣት ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል። በወላይታ ዞን  የግብረ ኃይሉ አባልና  የመንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፎላ እንደገለጹት  አሽከርካሪዎቹ የተቀጡት በአዋጁ ድንጋጌ መሰረት 50 በመቶ የጭነት ልክ  ተላልፈው በመገኘታቸው ነው።ተላለፈው የተገኙት 700 አሽከርካሪዎች መሆናቸውን አመልክተው  በዚህም ከ330 ሺህ ብር በላይ እንዲቀጡ መደረጉን አስታውቀዋል።መንገድ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች ደንብ በሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባራቸውን  አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አሳስበዋል።

በዉጪ የሚገኙ ትውልደ  ኢትዮጵያዉያን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚዉል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ፡፡

በዉጪ የሚገኙ ትውልደ  ኢትዮጵያዉያን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚዉል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ፡፡ አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 በተለያዮ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም ከሚሲዮኖች ሰራተኞች ከ100 ሚሊዮን ብር  በላይ መሰብሰቡን የብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታዉቋል፡፡ድጋፉ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በውጭ በሚገኙ 60 ሚሲዮኖች መሰባሰቡ ተጠቁሟል፡፡ ድጋፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ እንዳርጋቸው ተረክበዋል።ሚኒስትሩ በዚህ  ወቅት ድጋፉ አገር በችግር ውስጥ ባለችበት ጊዜ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት በመሆኑ አመስግነዋል። በተለይ ራሳቸው ችግር ውስጥ ሆነው አገራቸውን እየረዱ ያሉ ወገኖች እንዲሁም ሚሲዮኖች እያደረጉ  ላለው  ድጋፍ  አድናቆታቸውን ገልጸዋል።በሀገር ዉስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ይሁን በዉጪ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን  ቫይረሱን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት […]

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ:: የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥንና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ በማለዳ ጎብኝተዋል። የአስኮ፣ የመርካቶና የአየር ጤና መናኸሪያዎች የአገልግሎት አሰጣጥን ነዉተዘዋውረው የተመለከቱት በጉብኝታቸውም ተገልጋዮችን ሹፌሮችና ሌሎችንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመከላከል ስለሚያደርጉት ጥንቃቄና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ የአነጋግረዋል።በተለይ በአገሪቱ የኮቪድ 19 ቨይረስን ለመከላከል በትራንስፖርት ውስጥ እየተደረገ ያለውን ጥንቃቄና የኬሚካል ርጭት ተመልክተዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ ድንጋጌ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።