loading
የሳይበር ጥቃቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይችላሉ -የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 25፣2014 በሕዳሴው ግድብ እና በከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች መክሸፋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለጸ። የሀገሪቱን ሰላም እና ዕድገት በማይፈልጉ ሀገራት የሚደገፍ ድርጅት የሕዳሴው ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል በማቀድ ‘ብላክ ፒራሚድ ዎር’ በሚል ስያሜ የሳይበር ጦርነት መክፈቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ተናግረዋል። የፋይናንስ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው እና እርስ […]

ኑ የአቅመ ደካሞችን ቤት እንስራ-ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በአዲስ አበባ የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት እንጀምራለን አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህንን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በአዲስ አበባ ለአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት የሚሆን የመደመር መንገድ መጽሐፍ ተሽጦ ካስገኘው ገንዘብ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን […]

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ለአሽከርካሪዎች የሰጠው ማስጠንቀቂያ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 የትራንስፖርት አገልግሎቱን በሚያስተጓጉሉ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስጠነቀቀ::የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር እጸገነት አበበ ለኢቢሲ እንደገለጹት፣ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድጋፍ ሰጪዎችን ጨምሮ በተመደቡበት የስምሪት መስመር በመገኘት በተቀመጠው የታሪፍ መጠን ብቻ አገልግሎቱን መስጠት ይገባቸዋል፡፡ በጥናት መመለስ […]

በኢትዮጵያ ፍትህ እንዲረጋገጥ ብዙ ስራዎች ይቀራሉ-ኢ.ሰ.መ.ኮ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ለሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡ ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የ10 ወር የሥራ  ክንውን ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕ እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች  ቋሚ  ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡ ኮሚሽኑ ባለፉት 10 ወራት ግጭት የተከሰተባቸው 65 ቦታዎችን መድረሱን፣ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 450 ሺህ ስደተኞችን የሚያስጠልሉ አስር […]

በጎዳና ላይ የሚኖሩ 9 ሺህ ህጻናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀል የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 በጎዳና ላይ የሚኖሩ 9 ሺህ ህጻናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀል የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ። ፕሮጀክቱ በኤስ. ኦ .ኤስ የህጻናት መንደር ኢትዮጵያ የሚመራ ሲሆን ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ፣ አዳማና ድሬዳዋ ከተሞች የሚተገበር ይሆናል። በኢትዮጵያ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ካደረጉ ከ150 ሺህ በላይ ህጻናት መካከል 60 ሺህ የሚሆኑት በአዲስ አበባ […]

ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ጉዳይ የቅርብ ተመልካች ሆና እንደማትቀጥል አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ጉዳይ የቅርብ ተመልካች ሆና እንደማትቀጥል አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ በቀጠናው የወደብ አማራጮችን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ ደመቀ ይህን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡ በማብራሪያቸው ወቅትም ይህ […]

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሃት ለዳግም ጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት እንዲያወግዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሃት ለዳግም ጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት እንዲያወግዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች አሸባሪው ህወሃት በትግራይ ክልል በአስገዳጅ ሁኔታ ነዋሪዎችን ከታዳጊ እስከ አዛውንት ለጦርነት እየመለመለ እንደሆነ በማጋለጥ ላይ ይገኛሉ ብሏል ሚኒስቴሩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ […]

በኢትዮጵያ የዲጂታል ግብይትን ማስፋፋት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 ኢትዮ ቴሌኮም እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳዳር ከሰባት ከተሞች ጋር ስምምነት አደረጉ፡፡ ተቋማቱ ስምምነቱን የፈጸሙት ከክልሎቹ የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣኖች ጋር ሲሆን ስምምነቱም የደንበኞችን ክፍያ በቴሌ ብር ማዘመን የሚያስችል ነው፡፡ በስምምነቱ የተካተቱት ከተሞች ሐረሪ፣ ባሕር ዳር፣ ፍኖተሰላም፣ እንጅባራ፣ ደሴና ኮምቦልቻ መሆናቸውን የባልደረባችን ባምላክ ወርቁ ዘገባ ያመለክታል፡፡ በተጠቀሱት ከተሞች የሚገኙ የውሀ አገልግሎት […]

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባው የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የተጠሪ ተቋማቱን የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጧል፡፡የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ባቀረቡት ሪፖርት፥ ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ 360 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ […]

የሰዎች ያለአግባብ መታሰር አሳስቦኛል- ኢሰመጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ከህግ አግባብ ውጭ ዜጎችን ማሰር እንዲቆም ጠየቀ፡፡ ጉባኤው አስቸኳይ ባለው መግለጫው የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ጠቅሶ የተያዙበት መንገድ ህጋዊ አለመሆኑንና ቤተሰቦቻቸውን ለእንግልት መዳረጉን አብራርቷል ጄኔራሉ ከሰው ጋር ቀጠሮ አለኝ ብለው ከቤታቸው እንደወጡ ሳይመለሱ መቅረታቸውንና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ለማወቅ በርካታ ስፍራዎችን ማዳረሳቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በመጨረሻም ባህርዳር ከተማ […]