loading
መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ

አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የበልግ አብቃይ አካባቢዎች መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል የብሔራዊ ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።   በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚቀጥለው አንድ ወር ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል ብሏል።   በኤጄንሲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም  እንደተናገሩት በኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ የአርሲና የባሌ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም የቦረናና የጉጂ ዞኖች ከመደበኛ […]

ሚኒስቴሩ አንድ እሽግ ለአንድ ሴት በሚል መርህ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንፅህና መጠበቂያዎችን ሊሰበስብ ነው

ሚኒስቴሩ አንድ እሽግ ለአንድ ሴት በሚል መርህ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንፅህና መጠበቂያዎችን ሊሰበስብ ነው።   የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስቴር ለ16ኛ ጊዜ በሚካሄደውና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሚዘጋጀው የ 5ኪ.ሜ. የሴቶች ሩጫ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችን ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናግሯል። ‹‹ እኔም የመሪነት ድርሻዬን እወጣለሁ›› በሚል መርህ በሚካሄደው በዚሁ ሩጫ ላይ የሚካሄደው የ አንድ እሽግ […]

ከ 10 የዓለማችን የተበከሉ ከተሞች ዉስጥ ሰባቱ የህንድ ከተሞች መሆናቸዉን አንድ ጥናት አመለከተ

ከ 10 የዓለማችን የተበከሉ ከተሞች ዉስጥ ሰባቱ የህንድ ከተሞች መሆናቸዉን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ መቀመጫዉን በኢዥያ ያደረገዉ ኤር ቪዥዋል ኤንድ ግሪን ፒስ የተሰኘዉ ተቋም ባወጣዉ ጥናት  ከተበከሉ የዓለማችን ከተሞችም 50ዎቹ የሚገኙት  በህንድ በፓኪስታን በባንግላዲሽና በቻይና መሆኑን አመልክቷል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ በህንድ ከኒዉደልሂ ደቡባዊ ምዕራብ 30 ኪሎሜትር ላይ  የምትገኘዉ ጉርጉራም የተባለችው ከተማ የዓለማችን አንደኛዋ የተበከለች ከተማ  ሆናለች፡፡ […]

ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረገፆች  ሲሰራጩ የነበሩ በርሃብ ክፉኛ የተጎዱ ሕጻናት እና ወላጆችን የሚያሳዩ  ምስሎች የጌዲዮ ተወላጆች ምስል መሆናቸው ተረጋገጠ

ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረገፆች  ሲሰራጩ የነበሩ በርሃብ ክፉኛ የተጎዱ ሕጻናት እና ወላጆችን የሚያሳዩ  ምስሎች የጌዲዮ ተወላጆች ምስል መሆናቸው ተረጋገጠ ፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ከኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ የተፈናቀሉት ለሞት የሚያሰጋ ረሃብ የጠናባቸው መሆናቸውን  አረጋግጫለሁ ሲል ለሸገር ራዲዮ ተናግሯል፡፡ አረትስ ቴሌቪዠን ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው የስልክ ግንኙነት በብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ስራ […]

የሱሉልታ ከንቲባ “ቤት እናፈርሳለን አላልንም” አሉ

የሱሉልታ ከንቲባ ወይዘሮ ሮዛ ዑመር አቤቱታ በማቅረብ ላይ የሚገኙት የሱሉልታ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት  በሰባት ቀን ይፈርሳል የሚል ቃል አልወጣንም ብለዋል። ከንቲባዋ  “በ7 ቀናት ማስረጃ አቅርቡ አልን እንጂ ይፈርሳል አልልንም” ይላሉ።አክለውም፦”ሁሉንም ነገር ጊዜ ወስደን፣ ከሕዝቡ ጋር ተነጋግረን፣ ተግባብተን ነው የምናደርገው” ብለዋል።አሁን ገና የማጣራት ሥራ ላይ ነን ያለነው። ይፈርሳል የተባለ ነገር የለም ” ሲሉ ነው ከንቲባዋ ለሸገር […]

የደንበጫው “የካናቢስ ፋብሪካ” ግንባታ እቅድ አነጋጋሪ ሆኗል

የደንበጫው ካናቢስ መድሃኒት ፋብሪካ እቅድ አነጋጋሪ ሆኗል። በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ወረዳ ሊገነባ ነው የተባለው የካናቢስ መድሃኒት ፋብሪካ ፍቃድ የሰጠው አካል የለም ተባለ። የደምበጫ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽህፈትቤት በፌስቡክ ገጹ የካናቢስ መድሃኒት ፋብሪካ በወረዳው ሊገነባ መሆኑን በመግለጽ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያሰራጨው ደብዳቤ እና የሰራው ዘገባ በማህበራዊ ሚዲያ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል። ጽህፈት ቤቱ አስቀድሞ […]