loading
የአየር ላንድ መንግስት ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ማስዋብ በሚል በላሊበላ የአረንጓዴ ብርሃን ዝግጅት አካሄደ

የአየር ላንድ መንግስት ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ማስዋብ በሚል በላሊበላ የአረንጓዴ ብርሃን ዝግጅት አካሄደ፡፡ ዝግጅቱ ቅርሶችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል። ያም ሆኖ የአንድ ምሽቱ ተግባር ከዚህ ቀደም ከተያዘውና ላሊበላን በዘላቂነት ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ከተባለው ፕሮጀክት ጋር አልገናኝ ማለቱ ለብዙዎች ጥያቄ ፈጥሯል ። የአርትስ ሪፖርተር ከስፍራው ያጠናቀረችው ዘገባ እንደሚያስረዳው። በያዝነው ወር አየርላንድ እና ኢትዮጵያም […]

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ 170ሺህ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል  የተባለ የ2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጸደቀ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ላሉ 170ሺህ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል  የተባለ የ2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጸደቀ።   ፈንዱን ያጸደቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ለወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ለመመደብ የቀረበ ረቂቅ ሰነድ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡   በዚህም መሠረት ዝርዝር ዕቅዶችን በማዘጋጀት እና ከወጣቱ ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት የጋራ […]

የጌዲዮ ተፈናቃዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አገኙ

የጌዲዮ ተፈናቃዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አገኙ።   የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም ጌዲኦ ዞን አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች የተጠለሉበት ቦታ በመገኘት ነው ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ያደረጉት። ለተፈናቃዮች የተደረገው ድጋፍ  ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለተጎጂዎች እንዲደርስ ለማስቻል የተፈናቃይ ተወካዮችና የዞኑ አመራሮች በተገኙበት ገደብ ከተማ ላይ […]

በታንዛንያ እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው

በታንዛንያ ታንጋ በሚባል ከተማ በሚገኝ ማዌይኒ በሚባል እስር ቤት የነበሩ 235 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅኅፈት ቤት አስታውቋል። ስደተኞቹን ኢትዮጵያውያን የመመለሱን ስራ  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሄራዊ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ተብሏል። ከ3 ቀናት በፊት በተመሳሳይ ቦታ የነበሩ 50 […]

መጋቢት 29 ይጀመራል የተባለው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራላልተወሰነ ጊዜ  ተራዘመ 

መጋቢት 29 ይጀመራል የተባለው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራላልተወሰነ ጊዜ  ተራዘመ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራዉ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን  ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ይጀመራል ተብሎ ዕቅድ የተያዘለት አራተኛዉ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል፡፡   ኮሚሽኑ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ በመጨረሻም አራተኛውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም […]

“በዛሬው እለት ቦሌ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር የቡድን ጸብ እንጂ የፖለቲካ ግጭት አይደለም ” የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

“በዛሬው እለት ቦሌ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር የቡድን ጸብ እንጂ የፖለቲካ ግጭት አይደለም ” የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን። በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር ተራ የቡድን ጸብ እንጂ ከፖለቲካ ግጭት ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በቡድን ጸቡ ተካፋይ የነበሩትን 231 ተጠርጣሪዎች በሙሉ […]

በእንግሊዝ የጦርሃይል ሙዚየም የተቀመጠው የአጼ ቴዎድሮስ ጸጉር በነገው ዕለት ለኢትዮጵያ ይመለሳል

የአጼ ቴዎድሮስን ጸጉር ለማስመለስ ጥረት መካሄድ የጀመረው ከረጅም ጊዜ በፊት ቢሆንም በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ከእንግሊዝ ብሄራዊ ሙዚየም ዳሬክተር ብርጋዴር ጀስቲን ማሴጄውስክ ጋር ከተወያዩ በኋላ በእንግሊዝ በኩል የአጼ ቴዎድሮስን ጉንጉን ለኢትዮጵያ ለመመለስ ስምምነት ላይ ተደርሷል። የሁለቱ ሃገራት ሃላፊዎች በዚህ ቅርስ የመመለስ ሂደት ላይ የንጉሰ ነገስቱን ክብር በሚመጥን መልኩ በሚካሄደው የሽኝት ስነስርዓት ላይ በሰፊው መክረዋል፡፡ […]

በቦሌው የቡድን ጸብ ተካፋይ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በሙሉ ተገቢው ምክር ተሰጥቷቸው መለቀቃቸውን ፖሊስ አስታወቀ

በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከስቶ በነበረው የቡድን ጸብ ላይ ተሳትፈዋል በማለት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች ሙሉ በሙሉ መልቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽን እና የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር ተራ የቡድን ጸብ እንጂ ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ እንዳራገቡት ከፖለቲካ ግጭት […]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ የከፍያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየደረግኩ ነው አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ የከፍያ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየደረግኩ ነው አለ። አዲሱ አሰራር ደንበኞች የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በዘመናዊ መንገድ ለመፈፀም የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ተግባራዊ ይሆናል በተባለው በዚሁ አዲስ የክፍያ አሰራር ተጠቃሚ የሚሆኑት የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ማለትም ሁሉም የኢንዱስትሪ ደንበኞች፣ የግል ድርጅቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሲሆኑ፤በተጨማሪም ማንኛውም […]

በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የካንሰር ህመሞችን ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በኢትዮጵያ እና በአጋር አካላት መካከል ተፈረመ

በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የካንሰር ህመሞችን ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በኢትዮጵያ እና በአጋር አካላት መካከል ተፈረመ፡፡ ስመምነቱ በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የኦንኮሎጂና ኬማቶሎጂ የካንሰር አይነቶችን ለማከም፣ ለመከላከልና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ለህክምና ባለሙያዎች መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡   ስምምነቱን የተፈራረሙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ሊያ ከበደ፣ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይርጉ ገ/ህይወት እንዲሁም […]