loading
በአፍሪካ ዋንጫ አልጀሪያ ወደ ጥሎ ማለፉ ስታልፍ፤ ኬንያ የመጀመሪያ ጨዋታውን አሸንፋለች፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ግጥሚያዎች እየተከናወኑ ሲሆን ምድብ B ላይ ትናንት በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካፈለች የምትገኘው ማዳጋስካር አሌክሳንድሪያ ላይ ቡሩንዲን 1 ለ 0 በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሏን አስፍታለች፡፡ የማርኮ ኢላይማ ሃሪትራ ብቸኛ ጎል ደግሞ በምድቡ አራት ነጥብ ላይ እንድትደርስ አግዟል፡፡ በቀጣይ ከምድቡ ማለፏን ለማረጋገጥ አስቀድማ ጥሎ ማለፉን ከተቀላቀለችው ናይጀሪያ ጋር ብርቱ ፉክክር ይኖራቸዋል፡፡ […]

በሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ለስምንተኛ ጊዜ በአውሮፓዊቷ ፈረንሳይ እየተሰናዳ የሚገኘው የፊፋ ሴቶች ዓለም ዋንጫ ውድድር የግማሽ ፍፃሜ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ለዋንጫ ለማለፍ የሚደረገው አንደኛው ጨዋታ በግሮፓማ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አሜሪካ መካከል ይከናወናል፡፡ ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ለዋንጫው የታጩ ቢሆንም አንዳቸው ጉዟቸው እዚህ ላይ ሊገታ ግድ ይላል፤ ሁለቱም ቡድኖች ከምድብ ጀምሮ በጥሎ ማለፍ እና ሩብ ፍፃሜ […]

በኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

የ2019 የኮፓ አሜሪካ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ዙር ላይ የደረሰ ሲሆን ዛሬ ከዕኩለ ሌሊት በኋላ በእኛ ሰዓት አቆጣጠር 9፡30 ሲል በሁለቱ ታላቅ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት አርጀንቲና እና ብራዚል መካከል ይከናወናል፡፡ ጨዋታው ቤሎ ሆሪዞንቴ በሚገነው በእስታዲዮ ሚኔሮ ሲደረግ ደስ ሚል የውድድር ጊዜ እያሳለፈች የምትገኘው አርጀንቲና በብራዚል ድል ልትደረግ እንደምትችል እየተዘገበ ይገኛል፡፡ በኮፓ አሜሪካ 2019 ሩብ ፍፃሜ፤ የውድድሩ […]