loading
በዋሽንግተን ሲካሄድ በቆየው የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በዋሽንግተን ሲካሄድ በቆየው የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ:: በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከበድር ኢትዮጵያ እና ከኡስታዝ ጀማል በሽር (የአባይ ንጉሶች መስራች) ጋር በመሆን በGoFundMe ሲያካሂድ የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የማጠናቀቂያና የምስጋና ምሽት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከናውኗል:: በወቅቱም አምባሳደር ፍጹም […]

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ10 ሺህ 804 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሺህ 95 ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል።13 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን፤ 532 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና […]

ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013 ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ:: የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ አለ ፡በከተማዋ አስተዳደር የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት በትምህርቱ መስክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና ለከተማው ነዋሪ የስራ እድል ከመፍጠር እረገድ ሚናቸዉ ላቅ ያለ […]

ያለምንም የፖለቲካ ልዩነት ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ መቆም አለብን-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013  ዜጎች ያለምንም የፖለቲካ ልዩነት ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ መቆም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የኢዜማ ፓርቲ  አመራርና አባላት “ደሜን ለእናት ሀገሬ” በሚል መሪ ሃሳብ በብሔራዊ ደምባንክ በመገኘት ደም ለግሰዋል። የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተዘጋጀው ፓርቲው ለሀገሩ ህልውና መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው […]

በትግራይ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ናቸው::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013 አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት 7 ሺህ ያህል ትምህርት ቤቶች በከፊልና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ። ይህ የተገለፀው ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አሸባሪው ቡድን በትግራይ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችንና ከ48 ሺህ በላይ መምህራንን ከትምህርት ስርዓት […]

በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ እንደነበረ መግለጻቸውን ኢትዮጰያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። ይሁን […]

በመጪው የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በመጪው የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ፡፡ ከ26 ዓመታት በፊት ጀምሮ በየአምስት ዓመቱ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ የሚደረግ ሲሆን ለስድስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታም ከ2014 ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ይተገበራል። ነባሩ ስርዓተ ትምህርት የጥራትና አግባብነት እንዲሁም የሰው ሀብት ሰብዕና ግንባታ ጉድለቶች እንደነበሩት በጉባኤው ላይ ተነስቷል፡፡ ከቅድመ አንደኛ […]

ፈረንሳይ 10 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለአፍሪካ ልትሰጥ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 የፈረንሳይ መንግስት በሰጠው መግለጫ ክትባቱ በአፍሪካ ህብረት የክትባት ማግኛ ትረስት በኩል ለህብረቱ አባል ሀገራት ይከፋልል ብሏል፡፡ እስከ መጭው መስከረም ወር 2022 ድረስ 400 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ የክትባት መጠን ግዥ መፈጸሙን የፕሬዚደንት ማክሮን ጽህፈት ቤት ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በርሊን ላይ በተካሄደ ኮንፈረንስ የአፍሪካ መሪዎች ለአህጉሩ በቂ የክትባት መጠን እንዲሰጥ […]

አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ መካተታቸው ተገለፀ፡፡ በየዓመቱ 100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ስም ዝርዝር የሚያወጣው አቫንስ ሚዲያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ 4 ኢትዮጵያዊያን በስኬታማና ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካዊያን ሴቶች መዝገብ ውስጥ አካቷቸዋል። ከፕሬዚዳንቷ […]

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት – የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት ሲሉ የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። በወቅቱም የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት […]