loading
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይህን ያሉት ለሁለት ቀናት ወደ ኤርትራ ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር በአስመራ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው:: ሁለቱ መሪዎች በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ተያያዥ ጉዳዮች […]

ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና ተረከበች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና መንግስት ተረከበች። በኢትዮጰያ የቻይናው አምባሳደር ዣሆ ዢያን ኢትዮጵያ ቻይና በኮቪድ19 በተጠቃች ጊዜ ወዳጅነቷን ያሳየች ጠንካራ አጋር መሆኗን ተናግረዋል። አምባሳደሩ በቀጣይም ቻይና መሰል ድጋፎችን ታደርጋለችም ነው ያሉት፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ቻይና ዛሬ ካደረገችው ድጋፍ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የኮቪድ19 መከላከያ […]

ዳያስፖራው ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 ዳያስፖራው ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ፡፡ ዳያስፖራው ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓም መቀመጡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና […]

ፈረንሳይ በማሊ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት 19 ያልታጠቁ ንፁሃን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ!

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርመራ ቡድን እንዳረጋገጠው ፣ ባለፈው ጥር ወር ፈረንሳይ በማዕከላዊ ማሊ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት 19 ንፁሃንን ገድላለች፡፡ በተ.መ.ድ በማሊ ልዑክ እንዳስታወቀው ከሣተላይት በተገኙ ምስሎችና ከ 400 በላይ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ በመስራት የተዘጋጀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ፈረንሳይ ሪፖርቱን አስተባብላለች፡፡ በማሊ በ 2012 ሰሜናዊ ክፍል የጂሃዲስቶች ጥቃት […]

የፖለቲካ ቀውስ እና የኩቪድ 19 ወረርሽኝ ቦልሶናሮን አስጨንቋቸዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 የፖለቲካ ቀውስ እና የኩቪድ 19 ወረርሽኝ ቦልሶናሮን አስጨንቋቸዋል ተባለ:: የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ከዚህ ቀደም ብራዚላውያን ስለ ኮቪድ -19 ማልቀስ ማቆም እንዳለባቸው ሲናገሩ ነበር ጃየር ቦልሶናሮ የጦር ኃይሎች ፣ የባህር ኃይል እና የአየር ኃይል ሀላፊዎች በሙሉ ቸል ባሉበት በዚህ ወቅት አገሪቱ በየቀኑ ከፍተኛ የኮቪድ -19 የሞት ቁጥር እያስመዘገበች […]

አራት ተጠርጣሪዎች ከተሰረቁ የመኪና መለዋወጫዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2013 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለልማት በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ በተደረገ አሰሳ አራት ተጠርጣሪዎችን ከተሰረቁ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ክልል ልዩ ቦታ አሜሪካ ግቢ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው። መንግስት ለልማት ብሎ ባዘጋጀቸው ቦታዎች […]

አምብሮ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች ትጥቅ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት አራዘመ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2013 አምብሮ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድኖች ትጥቅ ለማቅረብ የሚስችለውን ስምምነት ለአራት ዓመታት አራዘመ።አምብሮ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ይፋዊ የቴክኒካል ስፖንሰር በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። በአዲሱ ስምምነት መሰረትም አምብሮ ኩባንያ ለወንዶች ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና ለታዳጊ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች ሙሉ የጨዋታ […]

የ533 ሚሊየን ፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ በነፃ በበየነ መረብ ተለቀቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 በመረጃ መረብ ጠላፊያዎች የፌስቡክ መረጃዎቻቸው ከተጠለፈባቸው 533 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መካከል ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኢትዮጵያ መሰረታቸውን ያደረጉ የፌስቡክ አካውንቶች ናቸው ተብሏል። የመረጃ ጣለፊያዎች ከፌስቡክ የዘረፉት የግለሰቦች መረጃ በነፃ በጠላፊዎች ህዝባዊ ፎረም ላይ እንደሚገኝ ነው ብሌፒንግ ኮምፒዩተር የዘገው። ይህ የተሰረቀ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠላፊዎች ለአባላቱ መሸጥ […]

ኢዜማ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ችግር ያቃልላሉ ያላቸውን 138 ቁልፍ ግቦችን የያዘ የቃል ኪዳን ያለውን ሰነድ ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 ፓርቲው በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመዲናዋ ነዋሪዎች ሊሰሩላቸው ይገባሉ ብሎ የለያቸውን 138 ቁልፍ ግቦች አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት ‘‘ኢዜማ እውነተኛ ፌዴራሊዝም መሰረቱ ያልተማከለ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ነው’’፡፡አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ብትሆንም በቅድሚያ ለሚኖሩባት ዜጎች ምቹ ሆና እንድትገኝ ማድረግ ይገባናልም ብለዋል። “ፓርቲው ከሕዝቡ ጋር ወርዶ ባደረገው […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሊጀምሩ ነው::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሊጀምሩ ነው::ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ከነገ ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃንማድረግ እንደሚችሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምረጡኝ ዘመቻቸው የሚጠቀሙበት ነፃ የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ እጣ ድልድል መርሐ-ግብር ተከናውኗል፡፡ ድልድሉ 25 በመቶ ለፓርቲዎች በእኩል ክፍፍል የሚሰጥ ሲሆን፣ በስራ ላይ ባሉ […]