loading
በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለፋና እንደተናገሩት ፥ አዲስ የሚገነባውን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። አውሮፕላን ማረፊያውን ለመገንባት የሚያስፈልገውን የቦታ ጥያቄ ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልል ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑን አቶ ተወልደ ተናግረዋል። ሊገነባ የታሰበው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ […]

ኢትዮጵያ የአጼ ቴዎድሮስን ሹርባ ከእንግሊዝ ለማስመለስ ጥያቄ አቀረበች፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1868 መቅደላ ላይ በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል በተደረገው ጦርነት የእንግሊዝ ወታደሮች ከዘረፏቸው ቅርሶች መካከል የአጼ ቴዎድሮስ ሹርባ ይገኝበታል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የንጉሱ ጉንጉን ጸጉር ለንደን ውስጥ በናሽናል አርሚ ሙዚየም ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ባለፈው ሚያዚያ ወር የአትዮጵያ አምባሳደር ሙዚየሙን ከገጎበኙ በኋላ የይመለስን ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ለጊዜው ለጎብኝዎች እይታ ከተቀመጠበት ቦታ ገለል ተደርጓል ሲል ዘ ጋርዲያን […]

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች 29 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የቻይና መንግስት የሰጠውን ነፃ የትምህርት እድል አገኙ፡፡

ዥንዋ እንደዘገበው ተማሪዎቹ በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን የሚከታተሉ ሲሆኑ ከ29 ተማሪዎች ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችም ይገኙበታል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያዉያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሰጠው ነፃ እድል በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የዲፕሎማሲ፣ የባህል እና የምጣኔ ሃብት ትስስር ያመለክታል ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይም […]

በትግራይ ክልል በመኾኒ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 425 ተቀጣጣይ ፈንጅ ተያዘ።

ተቀጣጣይ ፈንጁ 75 ኪሎ ግራም ክብደት ሲኖረው መኾኒ ከተማ ልዩ ስሙ ገረብ አባ ሃጎስ በተባለ ስፍራ የተያዘ ነው ተብሏል። ፈንጁ ድልድይ ስር ተደብቆ ወደ መቐለ ከተማ ሊሻገር ሲል በህዝቡ ጥቆማ መያዙንም የትግራይ ክልል የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።ፋና እንደዘገበዉ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛሉ፡፡

የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለድሉ ጅማ አባጅፋር እ እንደ ኦኪኪ አፎላቢ እና መሰሎቹ ወደ ሌላ ክለብ ማምራታቸውን ተከትሎም የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት እስካሁን በአጠቃላይ 11 ያህል ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡ በትላንትናው ዕለትም ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተሰናበቱት አሉላ ግርማ እና ዘሪሁን ታደለ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቡናው አስቻለው ግርማ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሁነዋል። ወደ ዋናው […]

በኢንዶኔዥያ ርእደ መሬት ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ፡፡

ሎምቦክ በተባለችው ደሴት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ400 ሰዎች በላይ ህይዎታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡ ቻናል ኒውስ ኤዥያ እንደዘገበው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ድረስ ከፈራረሱ ህንጻዎች ስር የተቀበሩ ሰዎችን የማፈላለጉን ስራ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የኢንዶኔዢያ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ሱቶፖ ፑሮ ኑግሮሆ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መረጃ 436 ሰዎች ሲሞቱ 1 ሽህ 300 የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡ […]

ካናዳ የሊቢያ ምርጫ ህገ መንግስቱን ተከትሎ መከናወን አለበት አለች፡፡

አናዶሉ የዜና ወኩል እንደዘገበው ሊቢያ የምታካሂደው የፓርላማና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌውን ተከትሎ መከናወኑ ስላለው ጠቀሜታ ተሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በሊቢያ የካናዳ አምሳደር ሂላሪ ቻይልደስ አዳምስ እና የሊቢያ ፕዝዳንታዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፋይዝ አል ሳራጅ ባረጉት ምክክር ነው ስምምነት ላይ የደረሱት፡፡ አምባሳደሯ እንዳሉት ሀገራቸው በሊቢያ ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠውን መንግስት ለመደገፍ ዝግጁ ነው፡፡ […]

የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ኢብኮ ዘግቧል፡፡ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ፣ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡ ልኡካኑ አዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዲሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የአፋር ብሄራዊ […]

ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ […]