loading
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነዉ፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበዉ አትሌት ፈይሳ በቅርቡ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ሀገር ቤትለመመለስ ወስኗል፡፡ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደ ሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸዉ ይታወሳል፡፡በወቅቱም ለአትሌቱ የጀግና አቀባባል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2010 በጀት ዓመት ካቀድኩት ማሳካት የቻልኩት 49.5 በመቶ ብቻ ነዉ አለ፡፡

አገልግሎቱ ለ468 ሺህ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ለማዳረስ አቅዶ ለ231 ሺህ 781 ደንበኞች ብቻ ነው ኤሌክትሪክ ማድረስ የቻልኩት ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2010 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2011 በጀት አመት ዕቅድን ዛሬ ባቀረበበት ወቅት የተቋሙ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ብዙወርቅ ደምሰዉ ኃይል በማምረት ደረጃ ሰፊ ስራዎችን ማከናወን ቢችልም ለተጠቃሚዎች በማዳረስ ረገድ […]

የአማራ ክልል ልዑክ በአስመራ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ጋር ምክክር ጀመረ፡፡

አዴኃንና የአማራ ክልል መንግስት የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይታቸዉ ሀሳብ ነዉ፡፡ አዴኃን ወደ ሀገሩ ገብቶ በሰላም እንዲንቀሳቀስና ጥሩ አጋር ሆኖ እንዲሰራ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግለትም ገልጧል ልዑኩ፡፡ የልኡኩ አባል የአማራ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኤርትራ መንግስት ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ያሳየውን አጋርነት ማድነቃቸዉን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡ የኤርትራ ውጭ […]

በምስራቅ ጎጃም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፋና ዘግቧል። ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ አደጋው የደረሰው ነሃሴ ነሀሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት አካባቢ ነው። በመሬት መንሸራተት አደጋውም የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ፥ ሁለቱ ደግሞ ስራ […]

የኦሮሚያ የከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በ2011 በጀት ዓመት ስራ አጥና በግል ስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች 3.283 ቢሊዮን ብር ለመስጠት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

በዚህም 1.1 ሚሊዮን ወጣቶችን በ90 ማህበራት ለማደራጀት ተወስኗል፡፡ ከነዚህ መካከል 64 ሺህ የሚሆኑት ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ናቸው፡፡ ለመፍጠር በተዘጋጀው የስራ ዕድል 52205 ሄክታር የከተማና የገጠር መሬት ተዘጋጅቷል፡፡ እንዲሁም 4648 አዳዲስ ሼዶች የሚገነቡ ይሆናል፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በወቅቱ እንዳሳወቁት ወጣቶች የተፈጠረላቸውን የስራ ዕድል ብቻ ሳይሆን በሃገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ […]