loading
ትላንት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስራ አስፈጻሚ ሆነዉ የተሾሙት ዶክተር አብርሃም በላይ ማን ናቸዉ?

አርትስ 18/12/2010 ዶክተር አብርሃም በላይ በ1972 ዓ.ም በአዲግራት የተወለዱ ሲሆን ፤ከ1991 ጀምሮ የኢፌድሪ መከላከያ ስራዊት አባል በመሆን እስከ ሌተናል ኮሌኔል ማዕረግ ደርሰዋል፡፡ከ1996-1998 ዓ.ም የመከላከያ ኢንጂነሪነግ ኮሌጅን በአሰተማሪነት አገልግለዋል፡፡ ከ19 98 ዓ.ም ጀምሮም በተለያዩ ሀላፊነቶች በኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግለዋል፡፡ ከ2007-2009 ባለዉ አመት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ የሀገር አቀፍ የምርምር ካዉንስል ቴክኒካል አማካሪ አባል በመሆንም ዶክተር አብርሃም […]

ለኢቢሲ ለውጥና እድገት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ዶክተር መረራ ጉዲና ገለጹ።

ከመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳች ደረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዶክተር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል በመሆን እያገለገለሉ ይገኛሉ። ዶክተር መረራ ወደ ሀላፊነት ከመጡ ጀምሮ በተቋሙ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸዋል። በተቋሙ ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚያሰራ ነው ያሉት ዶክተር መረራ  እስካሁን ከቦርድ አመራር አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት […]

ህንድ የአቡዳቢን እርዳታ አልፍልግም አለች፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ህንድ ያጋጠማትን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ 100 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ ለመለገስ ተዘጋጂታ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ህንድ ምንም እንኳ በአደጋው 400 ዜጎቿ ህይዎታቸውን ቢያጡና በሚሊዮን የሚቆጠሩት ቢፈናቀሉባትም እርዳታውን አልቀበልም ብላለች፡፡ የህንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ እንዳሳታወቀው የሀገሪቱ ፖሊሲ እንዲህ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋ ባጋጠመ ጊዜ የመልሶ ማቋቋሙን ሰስራ በራሷ አቅም እንድትወጣው ስለሚያስገድድ […]

የ 2010 የአሸንዳ በዓል ብዛት ያለዉ ቱሪስት የተገኘበት ነዉ ተባለ፡፡

አርትስ 18/12/2010 የዘንድሮዉ የአሸንዳ በዓል ከማነኛዉም ግዜ በበለጠ ከመላዉ አለም የመጡ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በስፋት የተሳተፉበትና ብዛት ያላቸዉ ኤርትራዊያን የተገኙበት መሆኑን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  ለአርትስ ቲቪ ገልጸዋል፡፤ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ስለነበርም ግብይቱ እንደተነቃቃ ነግረዉናል፡፡ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ አልባሳት ሽያጭም ከፍተኛ እንደነበር ሰምተናል፡፡ከተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎችም የመጡ የተለያዩ ብሄር […]

የደቡብ ኮሪያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞዋ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የእስር ቅጣት እንዲጨምር ወስኗል፡፡

የቀድሞዋ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝንት ፓርክ ጉን ሄይ በ2017 በሙስና ወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ በመባላቸው የ24 ዓመት አስራት ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በአልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቷ የእስር ጊዜያቸው እንዲቀንስላቸው አቤት ቢሉም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔው አንድ ዓመት አሳድጎ በ25 ዓመት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ፓርክ ከእስር በተጨማሪ ተጥሎባቸው የነበረው የገንዘብ ቅጣትም ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡ በዚህም መሰረት በታችኛው ፍርድ […]