loading
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ አዳማ ላይ እንደሚካሄድ ተገለፀ::

የምድብ ሀ አሸናፊ ባህርዳር ከነማ(የጣናው ሞገድ) ከምድብ ለ አሸናፊ ደቡብ ፖሊስ የሚያደርጉት የፍፃሜ የዋንጫ ጨዋታ አዳማ ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል፡፡ ይሄ ጨዋታ ቀድሞ በወጣው መርሃ ግብር ድሬዳዋ ላይ ይደረጋል የተባለ ቢሆንም የድሬዳዋ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት መታረሱ የቀንና የቦታ ለውጥ ለመደረጉ ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት የባህርዳር ከነማና የደቡብ ፖሊስ የዋንጫ ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ […]

አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በመጪው ቅዳሜ ጥዋት ወደ ኢትዮጵያ ይገባል፡፡

የአዲስ አበባ ብዙሃን መገናኛ እንደዘገበው የታማኝ በየነ ወደ ሀገሩ መመለስ ከግለሰብም በላይ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን እርሱን ለመቀበል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ገልጿል፡፡ አርቲስት ታማኝ በየነን ለመቀበል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለው ታማኝ በመጪው ቅዳሜ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል፡፡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ፣በብሄራዊ ትያትር ቤት እንዲሁም በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖሩ መርሃ ግብሮች […]

የኢትዮጵያ መንግስት ከዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ስምምነት ላይ ደረስኩ አለ::

ስምምነቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት፣ ከህብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበትና ዘላቂ ኑሮ የሚመሩበትን ሂደት ለመፈጸም የሚያስችል ነው ተብሏል። በስምምነቱ መሰረት በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤትም ተቋቁሟል:: ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፕሮጀክቱን ጽሕፈት ቤት እንዲመሩ አቶ ተስፋዬ ይገዙን መሰየማቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያ ንቅናቄ በአስመራ ከተማ በተለያዩ ጉዳዮች መወያታቸው ተገለፀ።

ፋና እነደዘገበው የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው፥ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አደም መሀመድ የሚመራው የመንግስት ልዑክና በትህዴን ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ የሚመራ ልዑክ በአስመራ መወያየታቸውን አስታውቀዋል። አርትስ 23/12/2010

የቀድሞው የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሀመድ ዑመር ፍርድ ቤት ቀረቡ ::

አቶ አብዲን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የቀድሞ የክልሉ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ራህማ ማህሙድ ሀይቤ ይገኙበታል፡፡ ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀን ጠይቋል፡፡ አቶ አብዲ መሐመድ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የብሔር ግጭት፣ በሃይማኖት መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል፡፡ ኢቢሲ እንደዘገበዉ አርትስ 23/12/2010

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ::

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሰራተኞቹ ለኢቢሲ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብሔር የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ ብሔር የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ ሪፖርተር እንደዘገበው የተሻሻለው መመርያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማንዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ብሔርን የሚጠቅስ በመሆኑ፣ ይህም ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎላ […]