በቡሪኪናፋሶ በቤተ ክርሰቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል
በቡሪኪናፋሶ በቤተ ክርሰቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል አልጀዚራ እንደዘገበው ጥቃቱ ከትላንት በስቲያ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ዲጂቦ አቅራቢያ በምገትኘው ሲልጋ ዲጂ ከተማ ነው የተፈፀመው፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመውም በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ላይ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያኑ ላይ በተፈጸመው ጥቃት አገልግሎት ላይ የነበረን አንድ ፓስተርን ጨምሮ በቤተ ክርስሰቲያን ውስጥ በፀሎትላይ የነበሩ 5 ምዕመናን ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በዚሁ ጥቃት ህይወታቸው ካለፈው አምስት ሰዎች በተጨማሪ ይህ ዘገባ እስከተሰራበት ጊዜ ድረስ ሁለት ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀም ተገልፃል፡፡ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪነፋሶ የሽብር ጥቃት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በቤተ ክርሰቲያን ላይ ጥቃቱ ሲፈፀም ይህ የመጀመሪያው ነው፣ የታጣቂዎች ማንነትም እስካሁን እንዳልታወቀ ነው አልጀዚራ በዘገባው ያሰፈረው፡፡