የኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት ይደረጋል፡፡
117ኛው የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ወይንም የስፔን ንጉስ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በነገው ዕለት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡ ግጥሚያው በባርሴሎና እና ቫሌንሲያ መካከል ሲቪያ ውስጥ በሚገኘው በሪያል ቤትስ ቤኒቶ ቪያማሪን ስታዲየም ይደረጋል፡፡ በአሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ የሚመራው የካታላኑ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው ተቀናቃኙን ሪያል ማድሪድ በደርሶ መልስ 4 ለ 1 ድል በማድረግ ለተከታታይ ስድስተኛ የፍፃሜ ጨዋታ ሲበቃ […]