loading
በአዲስ አበባ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ።

በአዲስ አበባ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ የከተማው ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ ለሚሳተፉ የአልሚ እና አማካሪ ድርጅቶች የከተማ አስተዳደሩ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው አስተዳደሩ በመንገድ ግንባታው ዘርፍ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከገንቢ እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ከመስራት በተጨማሪ ግንባታዎችን በሚያጓትቱ ድርጅቶች ላይ እርምጃ […]

በአማራ ክልል የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

በአማራ ክልል የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ አህመድ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ሠላማዊ ሆኖ እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ እና የተጠናከረ ጥበቃ ይደረጋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላትን ለመቆጣጠር […]

17ኛው የአርብቶ አደሮች በዓል በጂንካ ከተማ ሊከበር ነው።

17ኛው የአርብቶ አደሮች በዓል በጂንካ ከተማ ሊከበር ነው የኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮች በዓል “የአርብቶ አደሩ የላቀ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለአገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በጂንካ ከተማ እንደሚከበር ተገለጸ። ከጥር 15 እስከ 17 የሚከበረው ይኸው በዓል በደቡብ ክልል አዘጋጅነት በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ እንደሚካሄድም የሰላም ሚኒስቴር ገልጧል፡፡ ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ የማስፈፀም ብቃት ማነስ፤ […]

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን አፀደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን አፀደቀ። ምክር ቤቱ 19ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን፥ በውይይቱ በቀረቡለት ሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። በዚህም ምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና ዴሞከራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል። ረቂቅ አዋጁ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ […]

የሊቢያ ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን አፈረሱ።

የሊቢያ ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን አፈረሱ በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በተቀናቃኝ ሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት አምስት ሰዎች ሲገደሉ 20 የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡ ሬውተርስ የሀገሪቱን የጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው በተፋላሚ ሀይሎቹ መካከል ከአራት ወራት በፊት የተፈረመው  ተኩስ አቁም በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም አስገኝቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት 7ኛው ብርጌድ ወይም ካኒያት ተብለው በሚጠሩት እና ትሪፖሊ ፕሮቴክሽን […]

ሰርጌይ ላቭሮቭ ሶሪያን ለሶሪያዊያን እናስረክብ እያሉ ነው።

ሰርጌይ ላቭሮቭ ሶሪያን ለሶሪያዊያን እናስረክብ እያሉ ነው፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ሰሜናዊው የሶሪያን ክፍል ለበሽር አል አሳድ  መንግስት  ካላስተላለፍን በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም  ሊመጣ እንደማይችል ተረድተናል ብለዋል፡፡ ላቭሮቭ ይህን ያሉት አሜሪካ በሶሪያ ሰሜናዊ ድንበር አካባቢ በቱርክ መንግስት የሚተዳደር የፀጥታ ቀጠና ያስፈልጋል ማለቷን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ ቱርክ እና አሜሪካ ተመካክረው በሰሜናዊ ሶሪያ ድንበር የአንካራ መንግስት […]