loading
የጥምቀትን በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።

የጥምቀትን በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሮ የሚውለውን  የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ካሳሁን አያሌው እንደተናገሩት ከማይዳሰሱ ቅርሶች የሚመደበውን የጥምቀትን በዓል ወደ ቱሪስት መስህብነት ለመለወጥ ከወረዳዎች ጀምሮ እስከ ሚኒስቴር […]

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ያደረገውን ዝግጅት አጠናቅቆ ከዛሬው ከተራ በዓል ጀምሮ ወደ ስራ ገብቷል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በጋራ ስራ መጀመሩንም አስታውቋል። በዓላቱ በሰላም ተጀምረው […]

በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል 15 ሺህ ቱሪስቶች ይታደሙታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል 15 ሺህ ቱሪስቶች ይታደሙታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው በነገው ዕለት በጎንደር ከተማ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ለመታደም ከተለያዩ ሃገራት የመጡ 15 ሺህ አገር ጎብኚዎች እንደሚታደሙበት ተገልጿል። ይህንን እና በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች የሚካሄዱ የበዓሉን አከባበሮች ከጸጥታ ችግር የጸዳ ለማድረግ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቆ ወደስራ መግባቱንም የክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን […]

ስድስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለጨረታ ሊቀርቡ መሆኑ ተነገረ።

ስድስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለጨረታ ሊቀርቡ መሆኑ ተነገረ በኢትዮጵያ መንግስትና በግል አጋርነት የሚተገበሩ ስድስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናታቸው ተጠናቆ ለጨረታ ሊቀርቡ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚንስትር ዴኤታው ዶክተር ተሾመ ታፈሰ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት  መግለጫ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያቋቋመው ቦርድ በመንግስትና የግል አጋርነት ይተገበራሉ ብሎ ከለያቸው 16 ፕሮጀክቶች ውስጥ አስራ ሶስቱ የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክቶች […]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ውዝፍ ክፍያ ማስከፈል ጀምሬያለሁ አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ውዝፍ ክፍያ ማስከፈል ጀምሬያለሁ አለ የአገልግሎት ክፍያ በወቅቱ ካልከፈሉ ደንበኞች እስካሁን 340 ሚሊየን ብር መሰብሰቡንም ተናግሯል የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንደተናገሩት አገልግሎቱ ከዚህ በፊት ያልከተፈሉ ውዝፍ ክፍያዎችን ተከታትሎ እየሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ከሰበሰበው በተጨማሪ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ከደንበኞች ያልተሰበሰበ ውዝፍ ክፍያ አለኝ ይላል አገልግሎቱ። የማስከፈሉ ስራ መቀጠሉን […]

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ።

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ። በጉብኝቱ ወቅትም በትምህርት ቤቱ አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ እና በመፍትሄዎቻቸው ላይ ምክክር አድርገዋል። በውይይቱ ላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪዎች ወንበር እና የቤተ ሙከራ መሳሪያዎች እንዲሁም የህክምና ተቋም ቸግሮች ተነስተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው  በውይይቱ ወቅት በተነሱ ችግሮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር […]

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ቢሮ የላከው መግለጫ እንደሚያስረዳው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በንፁሃን ዜጎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል እና የምእራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በቅንጅት በሰሩት ስራ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ […]

የቱኒዚያ መንግስት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰራተኞቹ ጋር ተኳርፏል።

የቱኒዚያ መንግስት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰራተኞቹ ጋር ተኳርፏል በቱኒዚያ በተፅእኖ ፈጣሪነቱ የሚታወቀው ጀኔራል ሌበር ዩኒየን በመላ ሀገሪቱ መንግስትን ለመቃወም ባደረገው ጥሪ የአውቶቡስ፣ የባቡር እና የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ በሀገሪቱ መንግስት የሚተዳደረው ቱኒዚያ ኤየር የተባለው አየር መንገድ ነገሩ ሳይለይለት በረራ አላደርግም ብሎ ደንበኞቹ የጉዞ ፕሮግራማቸውን ለሌላ ቀን እንዲያዛውሩ በመንገር አሰናብቷቸዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች ፣ሆስፒታሎች እና ሌሎች የመንግስት አገልግሎት […]

የየመን ተዋጊ ሀይሎች እስረኞችን ለመለዋወጥ ውይይት ላይ ናቸው።

የየመን ተዋጊ ሀይሎች እስረኞችን ለመለዋወጥ ውይይት ላይ ናቸው ሁለቱ ወገኖች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አነሳሽነት ኦማን ላይ በሚወያዩበት ወቅት በሁለቱም በኩል የመግባባት መንፈስ ታይቷል ተብሏል፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት ሁለቱ ተዋጊ ሀይሎች በሁዴይዳ ወደብ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈራረሙ ካደረገ በኋላ ሳይውል ሳያድር ስምምነቱ ቢጣስም አሁንም የሰላም ስምምነቱ እንዲከበር እና እስረኞችን እንዲለዋወጡ ግፊት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት […]