loading
በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን የገባው ሁለት ኮንቴነር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቡድን በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ያስገባው ሁለት ኮንቴነር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። መነሻውን ከቱርክ ሜርሲን ወደብ ያደረገው ህገወጥ የጦር መሳሪያው፤ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ገብቶ በቁጥጥር ስር የዋለው፤ በወደቡ ለአምስት ወራት […]

የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጋር አብሮ እንዲውለበለብ የሚደነግገው አዋጅ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመራ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ አመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ነዉ  የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ ከአገራችን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ጋር አብሮ እንዲውለበለብ የሚደነግገውን ረቂቅ አዋጅ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የመራው፡፡ምክር ቤቱ የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀንን በሚመለከት የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ […]

ሶልቭ ኢት የተባለዉ የፕሮጀክት መተግበሪያ ሀሳብ ያላቸዉን ወጣቶች ለማበረታታትና ለወጣቶች እድልን ለማመቻቸት ያለመ መሆኑ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 በአንድ ሀገር የሰላም እጦት ሁነት  ሲበዛ ብዙ ምስቅልቅሎች ይፈጠራሉ፡፡ የአብዛኞቹ የሰላም እጦት  መነሻ ደግሞ ከወጣቶች  የስራ አጥነት ጋር ይያያዛል ፡፡የኢትዮጵያም ከዚህ የተለየ አይደለም ፡፡በኢትዮጵያም የስራ አጥነት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ አሁን ላይ የተማረዉ ያልተማረዉም  ወጣት ስራ አጥ መሆኑ የተለመደ ሆኗል፡፡ታዲያ ችግሩን ለመቅረፍ  ጥረቶች ቢደረጉም ከችግሩ ስፋት አንጻር  ለወጣቶች […]