loading
በእስር የሚገኙ 3 የሱዳን የቀድሞ ባለስልጣናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በእስር የሚገኙ 3 የሱዳን የቀድሞ ባለስልጣናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ:: በቫይረሱ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል ሁለቱ በዳርፉር በተፈፀመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉ ናቸው ተብሏል፡፡ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በቫይረሱ የተያዙት የኦማር አልበሽር ረዳት የነበሩት አህመድ ሀሮን፣ የመከላከያና የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የነበሩት አብደልራሂም ሞሀመድ ሁሴን እንዲሁም ምክትል […]

የአውፓ ህብረት ክሎሮኪን ኮሮናቫይረስን ለማከም ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 የአውፓ ህብረት ክሎሮኪን ኮሮናቫይረስን ለማከም ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደ:: የህብረቱ ኮሚሽን ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድሀኒት መጠቀም ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን አባል ሀገራቱ ክሎሮኪን እንዳይጠቀሙ አስጠንቀቋል፡፡የአውሮፓ ህብረት የመድኃኒት ባለሞያዎች ማህበር የአንዳንድ ሀገራት መሪዎች ዜጎቻቸው ረሮሎኪን እንዲወስዱ ሲመክሩ ከመታየታቸው ባለፈ ለኮቪድ 19 ውጤት ይኑረው አይኑረው በቂ ጥናት ተደርጎ ማረጋገጫ አልተሰጠውም ብሏል፡፡እስካሁን ሀይድሮክሲክሎሮኪን ለኮሮና ቫይረስ […]

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ሲገኙ የ1 ሰው ህይወት አለፈ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ሲገኙ የ1 ሰው ህይወት አለፈ :: ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4950 የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ተገኝተዋል፡፡አዲስ የተገኙትን ጨምሮ ባጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል፡፡ ትናንት ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የእድሜ ክልላቸው ከ 3 እስከ 70 ዓመት ሲሆን 53 […]

29ኛው የግንቦት 20 በዓል በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 29ኛው የግንቦት 20 በዓል በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል :: የግንቦት 20 የድል መታሰቢያ በዓልን በማስመልከትም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መድፍ ተተኩሷልጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም 29ኛው የግንቦት 20 በዓልን በማስመልከት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ግንቦት 20 የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት […]

በአዲስ አበባ ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ፊልድ ሆስፒታል ተገነባበአዲስ አበባ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ‘አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል ተገነባ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በአዲስ አበባ ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ፊልድ ሆስፒታል ተገነባበአዲስ አበባ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ‘አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል’ ተገነባ።በቅርቡ ሥራ የሚጀምረውን ሆስፒታል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የዓለም የምግብ መርኃ ግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ መርቀው ከፍተውታል።በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የሚገኘው ይህ የፊልድ ሆስፒታል 25 […]

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ ጀመሩ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ ጀመሩ :: በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉ እና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ጀምረዋል።በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ኤባ ሚጀና፣ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም ጅማ […]

ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች የሚሳተፉበት ቨርችዋል የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች የሚሳተፉበት ቨርችዋል የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ::መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የፊታችን እሁድ በአይነቱ ልዩ የሆነ  ቨርችዋል የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ መሆኑ ተገለጸመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ዲኤስቲቪ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት በሚደረገው ትግል ውስጥ የራሱን ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በመላው […]