loading
የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ዉጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡

154 ሺ 10 ወንዶችና 127 ሺ 964 ሴቶች በድምሩ 281 ሺ 974 ተማሪዎች ፈተናዉን ወስደዋል፡፡ ተማሪዎች ዉጤታቸሁን ለማወቅ በኤጀንሲዉ ድረ ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት admission በሚለዉ ዉስጥ የመፈተኛ ቁጥር በመጻፍ go የሚለዉን አንዴ በመጫን ማየት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ13 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ተመርምሮ፣ በየኮሌጆቹ አካዳሚክ ጉባኤዎች ተፈትሾና በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ ይሁንታ ያገኘውን መረጃ ተመልክቶ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡ በዚህም መሠረት፡-ፕሮፌሰር ተሾመ ሶሮመሳ፣ፕሮፌሰር አሰፋ ወልደማርያም፣ፕሮፌሰር ወርቅነህ ቀልቤሳ፣ፕሮፌሰር በቀለ አበበ፣ፕሮፌሰር ዳንኤል አሥራት፣ፕሮፌሰር ንጉሴ መገርሳ፣ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ለማ፣ፕሮፌሰር ጥላሁን ተክለኃይማኖት፣ፕሮፌሰር አበበ በቀለ፣ፕሮፌሰር ኃይሉ ወርቁ፣ፕሮፌሰር ሽመልስ አድማሴ፣ፕሮፌሰር ላይከማርያም አስፋውና ፕሮፌሰር አባተ ባኔ የሙሉ […]

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰማሩ 1 ሺህ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ገለጻ አድርገዋል

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ.ም የሚካሄድ ነው። ዛሬ ይፋ በተደረገው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 1 ሺ ተመራቂ ወጣቶች ተሳታፊዎች ናቸው። ወጣቶቹ ከሚኖሩበት ክልል ባለፈ ወደ ሌሎች ክልሎች በመሄድ በተለያዩ ተግባራት ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይህ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ […]

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውን ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለሙያ ጀሚ ኦርተን ገልጸዋል፡፡ ጀሚ ኦርተን ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ የእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑት ተማሪዎች በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው አምልካቾች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አመልካቾች ሁለት […]

አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ ከቀጣሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡

ይህ የሚሆነዉ በናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ነዉ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ጆብስ ጋር በጋራ በመሆን ˝ ናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ˝ በሚል የዘንድሮ አመት ስራ ፈላጊ ተመራቄዎችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሚገናኙበት መድረክ በሚሊኒየም አዘገጅቷል፡፡ የኢትዮ ጆብስ ሪጅናል ኮርዲኔተር ወ/ሮ ህሊና ለገሰ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ለመጀመሪያ ግዜ በተዘጋጀው አውደ ርዐዩ ቁጥራቸው አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች […]

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች 29 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የቻይና መንግስት የሰጠውን ነፃ የትምህርት እድል አገኙ፡፡

ዥንዋ እንደዘገበው ተማሪዎቹ በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን የሚከታተሉ ሲሆኑ ከ29 ተማሪዎች ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችም ይገኙበታል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያዉያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሰጠው ነፃ እድል በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የዲፕሎማሲ፣ የባህል እና የምጣኔ ሃብት ትስስር ያመለክታል ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይም […]

የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ ከተማ በባህር ዳር ሊገነባ ነው፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ከአሜሪካው ሀብ ሲቲ ላይቭ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ የመጀመሪያውን የቴክኖሎጂ ከተማ (Technology Hub City) ለመገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ የምክክር መድረኩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነገ ይካሄዳል፡፡ ምክክሩ Ethiopia is the Real WAKANDA በሚል ርዕስ እንደሚካሄድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በገፁ ፅፏል፡፡ የቴክኖሎጂ ከተማው በከፍተኛ ወጪ […]

አዲስ ይፋ የሆነው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ትምህርት ሚኒስቴርን ሦስት ቦታ የሚያደራጅ ነው::

አዲስ ይፋ የሆነው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ትምህርት ሚኒስቴርን በሦስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚያደራጅ መሆኑ ተጠቆመ። በትምህርት ዘርፍ አስተዳደር ላይ ማሻሻያ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጄይሉ ዑመር እንዳሉት ፍኖተ-ካርታው ብዙ መዋቅራዊ ለውጦችን የያዘ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር በሦስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲደራጅ የሚያደርግ ነው። በአዲስ መልክ የሚቋቋሙት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና […]

በትምህርት ሚኒስቴር ፍኖተ ካርታ ላይ የተካሄደዉ የሶስት ቀን ዉይይት ዉጤታማ እንደነበር ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ  በቲዉተር ገጻቸዉ ገለጹ፡፡

አርትስ 18/12/2010 ዶክተር ጥላዬ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የቀጣዩን 15 ዓመታት ፍኖተ-ካርታ ላይ በተደረገዉ ውይይት ፍኖተ ካርታዉን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ተገኝተዉበታል ብለዋል፡፡ ምኒስትሩ አሁን ያለዉ ፍኖተ ካርታ በረቂቅ ደረጃ መሆኑን ማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡