loading
በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መደፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መደፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከመዝገቦቹ ዉስጥ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው የ64 ዓመቱ ተከሳሽ በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታዉቋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታዉቋል፡፡ቢሮው ዘመቻውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ እድሜያቸው ከ9 ወር እስከ 5 አመት ለሆናቸው ህፃናት ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 2/ 2012 ዓ.ም ክትባቱ ይሰጣል፡፡የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ክትባቱ በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ጤና ተቋማት እና […]

ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች:: የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ካለፈው ፌብሯሪ ወር ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ 13 ዶክተሮቿ በኮቪድ 19 ሞተውባቸዋል፡፡ የኢራቅ የሀኪሞች ማህበር ሀላፊ አብዱል አላሚር አል ሺማሪ በመላ ሀገሪቱ ከ700 በላይ ዶክተሮች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ ሀኪሞቻችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመርዳት የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው […]

ኩባዊያን የህክምና ባለ ሞያዎች ኮቪድ 19 የመዋጋት ጥረተን ነለማገዝ ጊኒ ቢሳዉ ገቡ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 ኩባዊያን የህክምና ባለ ሞያዎች ኮቪድ 19 የመዋጋት ጥረተን ነለማገዝ ጊኒ ቢሳዉ ገቡ:: አስራ አንድ ዶክተሮችን ጨምሮ 21 አባላት ያሉት የህክምና ቡድኑ ወደ ኮናክሪ ያቀናው የጊኒ ቢሳዉ መንግስት ቫይረሱን ለመግታት ባስተላለፈው የእገዛ ጥሪ ነው ተብሏል፡፡ ይህም መንግስት ቫይረሱን ለመዋጋት ከሚከተላቸው ስትራቴጂዎች አንዱ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ባለስልጣናቱን ጠቅሶ እንደዘገበው […]