loading
ኒው ዚላንድ ከሀዘኗ መፅናናት ተስኗታል፡፡

ኒው ዚላንድ ከሀዘኗ መፅናናት ተስኗታል፡፡ በዚህች ሀገር  የተከሰተው በታሪኳ ታይቶ የማያውቀው የጅምላ ግድያ የብዙዎቹን ልብ በመሪር ሀዘን ሰብሯል፡፡ ይህ በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ግድያ ሳያንስ የሟቾቹ የቀብር ስነስርዓት መዘግየቱ ለቤተሰቦቻቸው ሌላ ተጨማሪ ሀዘን ሆኖባቸዋል፡፡ በሙስሊሞች ደንብ መሰረት አንድ ሰው በሞተ በ24 ሰዓት ውስጥ መቀበር አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ፖሊስ የሟቾቹን ማንነት ለይቸ አላጠናቀቅኩም በማለቱ ምክንያት እስካሁን ቤተሰቦቻቸውን […]

የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡ ክልሉ  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱና የታራሚዎች ቁጥር እንዲቃለል የማድረግ ርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዓለምሸት ምሕረቴ እንዳስታወቁት በየደረጃው ከሚገኙ ማረሚያ […]

ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች:: ይሄ ቁጥር የተገኘው በሶስት እስር ቤቶች በሚገኙ 1 ሺህ 736 እስረኞች ላይ በተደረገ ምርመራ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ከነዚህ ሶስት እስር ቤቶች መካከል ደግሞ 303 በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች የተገኙት በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ኦዋራዛቴ […]

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች:: የአማራ ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ግለሰቧ በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ የሀገራቸውን የፍትህ ስርዓት አጣጣሉ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ የሀገራቸውን የፍትህ ስርዓት አጣጣሉ::በሳምንቱ መጨረሻ ቀን በኢየሩሳሌም አውራጃ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው የክስ ሂደታቸውን የተከታተሉት ኔታኒያሁ የተከሰስኩት በሀሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡የክሱ ዋና ዓላማ ጠንካራውን ጠቅላይ ሚስትር ከስልጣን ለማውረድ ቢሆንም ይህ ግን አይሳካም በማለት ሀገራቸውን በታማኝነት መምራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ኔታኒያሁ እሳቸው የሚመሩትን የቀኝ ዘመም ፖለቲካ አራማጅ የሆነውን ሊኩድ […]

በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአሜሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ይዘት እየተላበሰ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአሜሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ይዘት እየተላበሰ ነው ተባለ:: አሁን ላይ የጥቁሮች ህይዎት ያሳስበናል የሚለው ተቃውሞ ከአሜሪካ ከተሞች አልፎ በእግሊዝ፣ በጀርመን በኒው ውዚ ላንድ እና በሌሎች ሀገራትም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በቅርቡ በፖሊስ መኮንን የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ በኮሮናቫይረስ ለምትታመሰው አሜሪካ ሌላ ራስ […]

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦኛል አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦኛል አለ፡፡ ድርጅቱ በሪፖርቱ እንደስታወቀው ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት 1 ሺህ 300 የሚሆኑ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸው ታወቋል፡፡ በተለይ ኢቱሪ፣ ሰሜንና ደቡባዊ ኪቩ አካባቢዎች የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት […]

በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ተባለ::በሴቶችና ህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በማስመልከት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት ላይ በሚገኙ ተቋማት በመገኘት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት :: ፤የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመከላከል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ትኩረታችን የቁጥር ጉዳይ ሳይሆን አንድም […]

በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መደፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መደፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከመዝገቦቹ ዉስጥ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው የ64 ዓመቱ ተከሳሽ በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ […]