loading
በኢትዮጵያ በኮሮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር  1 መቶ 11 ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር  1 መቶ 11 ደረሰ ::በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታዉቀዋል።ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ396 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ሶስት ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ሁሉም የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።ከዚህ ውስጥ የ11 እና የ15 አመት ታዳጊዎች […]

አለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ስጋት እንደተደቀነባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2012 አለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ስጋት እንደተደቀነባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።የአለም ምግብ ፕሮግራም ሃላፊ ዴቪድ ቤስሌይም በረሃብ ምክንያት የሚከሰተውን ከፍተኛ ቀውስ ለማስወገድ ፈጣን እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣ ሪፓርት በረሃብ ምክንያት ከ135 ሚሊየን እስከ 250 ሚሊየን ሰዎች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል አመልክቷል። የአለም ምግብ ፕሮግራም የረሃብ ስጋት […]

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1መቶ 16 ደረሰ ባጠቃላይ 21 ሰዎችም አገግመዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1መቶ 16 ደረሰ ባጠቃላይ 21 ሰዎችም አገግመዋል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በ 1 ሺህ 73 ሰዎች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በ2 ሰዎች ላይ መገኘቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸዉ ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን ወንዶች ሲሆኑ፤ የ22 ዓመቱ ሰዉ በአፋር ክልል ገዋኔ ነዋሪና የዉጭሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለዉ ሲሆን ጉዳዩ በመጣራት […]

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው የለም::

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው የለም:: ተባለ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ965 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን ነው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁት። ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ በተደረገው ምርመራም ቫይረሱ የተገኘበት ሰው አለመኖሩንም አስታውቀዋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ […]

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ  ሰዎች ቁጥር  25 ደረሰ፡፡

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ  ሰዎች ቁጥር  25 ደረሰ፡፡የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ  9 መቶ 33 ሰዎች ተመርምረዉ  በ1 ሰዉ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡ቫይረሱ የተገኘባቸዉ የ60 ዓመት ሴት ሲሆኑ ከእንግሊዝ የመጡና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ዉስጥ የነበሩ ናቸዉ፡፡በ24 ሰዓት ዉስጥ 4 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን ሁለቱ ከአዲስ አበባና ሁለቱ ከባህርዳር ናቸዉ፡፡ባጠቃለይ በለይቶ ማቆያ ህክምና ዉስጥ […]

የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ::

የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ:: የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የብረታብረት ፍሬም ሥራ 100 ፐርሰንት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የሲቪል ሥራው 87 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው ደግሞ 46 በመቶ መጠናቀቁን የሕዳሴው ግድብ ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ።ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ሥጋት በዓለም ላይ ጥላውን ያጠላ ቢሆንም […]

በዘንድሮው ዓመት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ::

በዘንድሮው ዓመት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ዘንድሮ የሚተከሉ ችግኞች ያሉበትን ደረጃ በጎበኙበት ወቅት ነዉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ሶደሬ አካባቢ በመገኘት ነው የችግኝ ማፍላት ስራውን ከክልሉ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር በመሆን የጎበኙት።በዘንድሮው አመት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፥ […]

ማንኛዉም ሰዉ ደም ለመለገስ ሲመጣ ፕሮግራም አሲዞ እንዲመጣ የሚያደርግ መተግበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የቢሄራዊ ደም ባንክ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 ማንኛዉም ሰዉ ደም ለመለገስ ሲመጣ ፕሮግራም አሲዞ እንዲመጣ የሚያደርግ መተግበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የቢሄራዊ ደም ባንክ አስታወቀ፡፡የደም ባንኩ ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ላይ የደም እጥረት ነበረ አሁን ላይ ግን በተሰራዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ታላቅ መነቃቃት መታየቱን ያስታወቀ ሲሆን የረመዳንን ፆም ምክንያት በማድረግ ሁሉም የብሄራዊ ደም ባንክ ቅርጫፎች እስከ […]

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደረሰ በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።ሚኒስትሯ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ943 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን በፌስ ቡክ ገጻቸው የገለጹ ሲሆን፤በዚህም አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል፡፡ቫይረሱ የተገኘበት የ45 አመት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው […]

የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ:: የትምህርት የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚመለከተው ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ኮሚሽንን 2ኛ ስብሰባ ተካሂዷል።በዚህም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆኖነዋል።በውይይቱም የኮረሮ ቫይረስ በትምህርትና ልማት ላይ በረጅም ጊዜ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ […]