loading
የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ::

የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ:: የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ቦርዶች ለሀገራት እና ኩባንያዎች ለለኮቪድ -19 መስፋፋት ለመከላከል ፣ ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ጥረት 14 ቢሊዮን ዶላር ለፈጣን ቁጥጥር ፋሲሊቲ እንዲጨምር ፈቀደ ፡፡በሳምንቱ መጨረሻ የዓለም ባንክ ለፈጣን ቁጥጥር 1ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በ 40 አገሮች ውስጥ ፕሮጀክቶችን እያዘጋጀ ነውም ተብሏል፡፡ በአፍጋኒስታን እና […]

በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ:: በናይሮቢ በተባበሩት መንግስታትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ማህበር (በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸዉን በኬኒያ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ የማህበሩ አባላት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ከመከሩ በኋላ ባወጡት የጋራ አቋም መንግስት […]

የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀየኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ጽ/ቤትም የበጀት ዓመቱ ለመጠናቀቅ በሚቀሩት ሶስት ወራት ውስጥ ለሚኖሩት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ወጪ በማብቃቃትና በቁጠባ በመጠቀም ከተመደበለት መደበኛ በጀት የሚቀነስ የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥም  አስታውቋል ፡፡ከዚህ በተጨማሪም  ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት መወሰናቸው   የፕሬዝዳነት […]

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012  በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት:: ኮቪድ 19 በአፍሪካ መዛመቱን ቀጥሏል፤ በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 200 በላይ ከፍ ብሏልየሀገሪቱ መንግስት ይፋ ባወጣው መረጃ በደቡብ አፍሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች 1 ሺህ 280 ደርሷል ነው የተባለው፡፡ደቡብ አፍሪካ ሁለኛውን ሞት ይፋ ያደረገች ሲሆን በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 31 የሚሆኑትን አክማ ማዳኗንም ተናግራለች፡፡የበሽታው […]

ፖፕ ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያስተላለፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012  ፖፕ ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያስተላለፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለዓለም ያስተላፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉት ተናግረው በዚም ዓለም በሙሉ አቅሟ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እንድትከላከል ያስችላታል ብለዋል፡፡ በዓለም እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ  በሚደረግ ጥረት ላይ ከፍተኛ […]

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ  ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት  ሰዎች መገኝታቸው ተረጋግጧል፡፡በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስት ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውም ታዉቋል፡፡የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ […]

የኮሮና ቫይረስ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሚኖሩባቸው መንደሮች እንዳይገባ ልንረባረብ ይገባል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሚኖሩባቸው መንደሮች እንዳይገባ ልንረባረብ ይገባል ተባለ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ  የኮሮና ቫይረስን  እና  የሕዳሴው ግድብ ግንባታን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት  አንደኛው  የሀገራችን ፈተና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ቫይረሱ የሚተላለፍበት መንገድ ከሰዎች ለሰዎች ንኪኪ ጋር የተገናኘ እና የሚስፋፋበትም መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ ፈጣን እየሆነ እንደመጣ በየዕለቱ የምናየው […]

የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 የአማራ ክልል መንግሥት 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ፡፡ ክልሉ  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ 7 ሺህ 650 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱና የታራሚዎች ቁጥር እንዲቃለል የማድረግ ርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዓለምሸት ምሕረቴ እንዳስታወቁት በየደረጃው ከሚገኙ ማረሚያ […]

Why Ethiopia’s Internet connectivity matters?

Why Ethiopia’s Internet connectivity matters? The Internet is an indispensable part of life in the developed world. Its impacts on all spheres of human life and work have been increasingly pervasive. African countries have lagged behind their Western and Eastern counterparts in relation to Internet connectivity. Many African countries are still struggling to create a […]

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 ደረሰ

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 ደረሰ አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ነዉ የጤና ሚኒስቴር የገለጸዉ፡፡የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።ቀሪዎቹ […]