loading
የኦሮሚያ ክልል ለፋሲል ከነማ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገበት ሚስጥር ይፋ ሆነ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር ሀላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለፋሲል ከነማ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገበት ሚስጥር ይፋ አደረጉ፡፡ አቶ አዲሱ በፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ እንደገለጹት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለፋሲል ከነማ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገበት ሚስጥር መታሰቢያነት ከአመታት በፊት አምባገነኑ […]

የሰብአዊ እርዳታ ከፍ እንዲል ካልተደረገ በትግራይ ከባድ የረሃብ አደጋ ሊከሰት ይችላል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 የሰብአዊ እርዳታ ከፍ እንዲል ካልተደረገ በትግራይ ከባድ የረሃብ አደጋ ሊከሰት ይችላል:: በትግራይ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል ዩናይትድ ኪንግደምና የተባበሩት መንግሥታት ስጋታቸውን ገለጹ ::በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በወራት ጊዜ ውስጥ የረሃብ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የዩናይትድ ኪንግደም ረሃብ የመከላከል ልዩ መልዕከተኛ የሆኑት ኒክ ዳየር አስጠንቅቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት […]

የአሜሪካ ኤምባሲና የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቀጠሮ አልያዙም::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 የአሜሪካ ኤምባሲና የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቀጠሮ አልያዙም:: የብሔራዊ ክብር በሕብር አስተባባሪ ኮሚቴ ከብሪታኒያ ኤምባሲ ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ:: ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም የተቋቋመው የብሄራዊ ክብር በህብር አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የብሪታኒያ ኤምባሲ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ […]

በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ::ከሁለት ዓመታት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው ::ከሁለት ዓመታት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው። አደጋው የደረሰበት የግምቢቹ ወረዳ ቱሉፈራና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ አራት ፕሮጀክቶችም ሊተገበሩ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ […]

ለሕዳሴዉ ግድብ የግንባታ ቁሳቁሶችን በወቅቱ ለማድረስ የትራንስፖርት እጥረት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013  የሕዳሴዉ ግድብ ሁለተኛ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የሲሚንቶና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን በወቅቱ ለማድረስ የትራንስፖርት ችግር መከሰቱ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለጸዉ  የታላቁ  የኢትጵያ  ህዳሴ ግድብ ሁለተኛውን የውሃ ሙሌት ለማሳካት የከባድ ጭነት ባለንብረቶች የ24 ሰዓት የስራ ርብርብ ተሳታፊ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን ጥሪ ባቀረበበት ወቅት ነዉ ሲሚንቶ እና ሌሎች […]

የአልሲሲ የጂቡቲ ጉብኝትና አጋር የማብዛት ስትራቴጂ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ከፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ለመምከር ወደ ጂቡቲ አቅንተዋል፡፡ ኢጂፕት ቱደይ በዘገባው እንዳስነበበው አልሲሲ ጂቡቲን ሲጎበኙ በግብፅ ፕሬዚዳንቶች ታሪክ የመጀመሪያው ሰው ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ የግብፅ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ባሳም ራዲ በሰጡት መግለጫ የአልሲሲ ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነትነ ማጠናከር ላይ የሚያጠነጥን […]

በናይጄሪያ የኮሌራ ወረርሽኝ ስጋት::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013  በናይጄሪያ የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ተከትሎ 20 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል በተከሰተ የኮሌራ በሽታ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የ20 ሰዎች ህዎት ሲያልፍ ከ300 በላይ ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል፡፡ ባውቺ በተባለችው ግዛት የተከሰተው የኮሌራ በሽታ በዘጠኝ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ መስፋፋት ማሳየቱን የግዛቷ ጤና ኮሚሽነር ሞሃመድ ሚጎሮ ገልፀዋል፡፡ አፍሪካ […]