loading
የደቡብ ዕዝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የዕዙ የሰራዊት አባላት ሆነው ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩ የሰራዊት አባላት ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013 የደቡብ ዕዝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የዕዙ የሰራዊት አባላት ሆነው ለአሸባሪው ህወሓት ሲሰሩ በነበሩ የሰራዊት አባላት ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የሰራዊት አባላቱ ለህገ-መንግስቱና ለሀገራቸው የገቡትን ቃል ኪዳን ወደጎን በመተው የሰራዊቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች አደጋ ላይ የሚጥሉና የትግራይ ልዩ ሃይልን የሚያጠናክሩ ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸው በችሎቱ ተነስቷል፡፡ በተለይም የሰራዊቱን ልዩ ልዩ ምስጢራዊ ሰነዶች ለትግራይ ልዩ […]

ህገወጥ ነጋዴዎችን በአከባቢያችሁ ለሚገኝ ፖሊስ ጠቁሙ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለንግድ ማህበረሰቡ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡ ቢሮው አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ በአቋራጭ ለመክበር እና ሆን ብሎ ህገ-ወጥ የዋጋ ጭምሪ እና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለመፍጠር ጥረት ማድረግ ላይ መሆናቸውን ድርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ስለሆነም በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ ተሰማርታችሁ የምትገኙ ነጋዴዎች ለሽያጭ በሚቀርቡ ማለትም በተለይ ከውጪ ሃገር […]

የኢትዮጵያ ሽልማት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013  በዓለም ፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ አዘጋጅነት ከዚህ በፊት በአሜሪካ ለሶስት ዙር የተካሄደው የኢትዮጵያ ሽልማት ለአራተኛ ግዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በጥር 2011 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ኮሎራዶ የተቋቋመው ዓለም ፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ሄልተን ነሀሴ 29፣ 2013 ዓ.ም በዕለተ ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ታዉቋል፡፡ […]

በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር ከዓለም ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013 በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር ከዓለም ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡በብሉምበርግ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የ82 ሃገራት ዝርዝር ውስጥ በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡ የሥራ አጥነት መጠኑ በሁለተኛው ሩብ ዓመት ከ32.6 በመቶ እስከ መጋቢት ባሉት ሦስት ወራት ድረስ ወደ 34.4 በመቶ ከፍ ማለቱን በፕሪቶሪያ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ሰታትስቲክስ የመረጃ […]