loading
በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ እንደነበረ መግለጻቸውን ኢትዮጰያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። ይሁን […]

በመጪው የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በመጪው የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ፡፡ ከ26 ዓመታት በፊት ጀምሮ በየአምስት ዓመቱ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ የሚደረግ ሲሆን ለስድስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታም ከ2014 ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ይተገበራል። ነባሩ ስርዓተ ትምህርት የጥራትና አግባብነት እንዲሁም የሰው ሀብት ሰብዕና ግንባታ ጉድለቶች እንደነበሩት በጉባኤው ላይ ተነስቷል፡፡ ከቅድመ አንደኛ […]

ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የሲዳማ ክልል ፖሊስ  ኮሚሽነር አበራ አሬራ ለኢዜአ እንደገለጹት፤  ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት  እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነው። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተካሄደ አሰሳ በሃዋሳ ከተማ በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ታቅዶ የነበረና የህትመት ሂደቱ ያላለቀ ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ […]

ፈረንሳይ 10 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለአፍሪካ ልትሰጥ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 የፈረንሳይ መንግስት በሰጠው መግለጫ ክትባቱ በአፍሪካ ህብረት የክትባት ማግኛ ትረስት በኩል ለህብረቱ አባል ሀገራት ይከፋልል ብሏል፡፡ እስከ መጭው መስከረም ወር 2022 ድረስ 400 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ የክትባት መጠን ግዥ መፈጸሙን የፕሬዚደንት ማክሮን ጽህፈት ቤት ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በርሊን ላይ በተካሄደ ኮንፈረንስ የአፍሪካ መሪዎች ለአህጉሩ በቂ የክትባት መጠን እንዲሰጥ […]