loading
በኢትዮጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በኢትዮጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ:: በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል፡፡ ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች […]

በመዲናዋ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በመዲናዋ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ:: በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ አመት ውስጥ 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ፕሮፐርቲ 2000 ደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ ተፈራርመውታል፡፡ ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን […]

በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ::በአዲስ አበባ የሚገኙ 2 ሺህ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ያህል ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አካል ጉዳተኞች የእውቅና መርሃ ግብር […]

ከአሜሪካ ጋር ያጋጠመንን ጉዳይ በወዳጆቻችን በኩል ለመፍታት እየሰራን ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013  ከአሜሪካ ጋር ያጋጠመንን ጉዳይ በወዳጆቻችን በኩል ለመፍታት እየሰራን ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ:: የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ አቋሟን ትቀይራለች ብሎ እንደሚያምንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ ገልጸዋል:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ጋዜያዊ መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ፣ ከአሜሪካ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት የመግለጫቸው ዋነኛ […]

ኢሚግሬሽን “ለትግራይ ተወላጆች አገልግሎት መስጠት አቁሟል” መባሉን “ውሸት ነው” አለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለትግራይ ተወላጆች የሚሰጠውን አገልግሎት አቁሟል በሚል በማህበራዊ ሚድያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ “ፍጹም ሀሰት” እንደሆነ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዪኒኬሽን ዳይሬክተር ደሳለኝ ተሬሳ ተናገሩ፡፡ አቶ ደሳለኝ ለአል-ዐይን እንደተናገሩት በክልሉ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት “ትግራይ” የሚለው ስም ከኤጀንሲው የአገልግሎት ማመልከቻ ድረገጽ ወጥቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ለትግራይ ተወላጆች […]

የባልደራስ እና የምርጫ ቦርድ የችሎት ክርክር::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 ምርጫ ቦርድ ሰበር ችሎት ለባልደራስ የወሰነውን ለምን እንዳልፈጸመ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ (3 አባላት) በዕጩነት እንዲመዘገቡ የሰጠውን ውሳኔ ለምን መፈጸም እንዳልቻለ የሚያስረዳዉም ሐሙስ ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ለቦርዱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው […]

የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጉብኝት ለኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲ ያለዉ ፋይዳ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013  የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጉብኝት ወቅታዊውን የኢትዮ-አሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሊያለዝበው ይችላል ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር በዕውቀቱ ድረሰ ተናገሩ፡፡ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉን ባስታወቀ ማግስት ድርጊቱን የኦክላሃማው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡ ሴናተሩ በሀገራቸው ሳሉ ከሚያሳዩት የኢትዮጵያ አጋርነት ሌላ ከሰሞኑ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ መግባታቸዉ […]

ዶላር እናበዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችን የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 ዶላር እናበዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችን የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ:: በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዶላር እናባዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ‘ሲኤምሲ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ዶላር እናባዛለን በማለት የአካባቢውን […]

የውጪ ሃይሎች ከህዳሴው ግድብ እና ከሉአላዊነታችን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ጥሪ የሚቀርብበት ሀገር አቀፍ የምሁራን መድረክ ሊካሄድ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013  የውጪ ሃይሎች ከህዳሴው ግድብ እና ከሉአላዊነታችን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ጥሪ የሚቀርብበት ሀገር አቀፍ የምሁራን መድረክ ሊካሄድ ነው:: የጎንደር ዩንቨርሲቲ ይህን ዓለም አቀፍ ጥሪ የሚቀርብበትን መድረክ በመጪው ሃሙስ ለማካሄድ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የዩንቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን ለኢዜአ እንደገለጹት ሀገር አቀፉ የምሁራን መድረክ አላማ የውጪ ሃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ […]

በቡርኪናፋሶ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት ብዙዎች ህይወታቸዉ አለፈ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013  በቡርኪናፋሶ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የሟች ቁጥር ከ130 በላይ መድረሱ ተሰማ  መረጋጋት በተሳነው ምእራባዊ የሀገሪቱ ክፍል የ132 ሰዎችን ህይዎት የቀጠፈውን የታጣቂዎች ጥቃት የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፅኑ አውግዞታል፡፡ ታጣቂቂዎች ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ጥቃቱን ያደረሱት ዮጋ ተብላ በምትጠራው ግዛት በምትገኘውና ከኒጀር ጋር በምትዋሰነው የሶልሃን መንደር ነው፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት […]