loading
የቱርክ የፊልም ኢንዱስትሪም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን እያጠናከረ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013 የለውጥ ሂደቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያና ቱርክ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በጋራ እየሰሩ ነው:: ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ተጨማሪ  ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። በቱርክ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በመግለጫቸው ሁለቱ አገሮች ያላቸው ግንኙነት ወንድማማችነት ነው ብለዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው […]

ህወሓትን ሲደግፉ የነበሩ ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ ከኢንተርፖል ጋር እየሰራን ነዉ-ፌደራል ፖሊስ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013  ለአሸባሪው ህወሓት የኢኮኖሚ ምንጭ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ 117 የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ህገወጥ ምንዛሪን አስመልክቶ ለአርትስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለሽብር ቡድኑ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአሸባሪው ቡድን የፋይናንስ ምንጭ […]

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊዎች የቡሄ በዓልን በማስመልከት ለህዳሴ ግድብ ገንዘብ አሰባሰቡ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013  በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊ ኢትዮጵያዊያን የቡሄ በዓልን በማስመልከት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አካሄዱ በፕሮግራሙ ላይም በቡሄ ጭፈራ የታጀቡ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ ታዳጊዎቹ ካስተላለፏቸዉ መልዕክቶች ውስጥ የግድቡ መጠናቀቅ ህጻናትና ታዳጊዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ያስችላቸዋል የሚለው ይገኝበታል፡፡ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መረጃውን ያጋሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ የሁሉም […]

የአሸባሪው ጌታቸው ረዳ ወንድም ሃይለ ረዳ መልዕክት፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14፣2013 አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ እንቅስቃሴ የአገር ክህደት መሆኑን የጌታቸው ረዳ ወንድም ሃይለ ረዳ ገለጹ:: በአፋር ክልል ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ ዜጋ መምህሩ ሃይለ ረዳ፤ አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ን ህዝብ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ደም ለማቃባት ትንኮሳ ማድረጉ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲሉም ገልጸዋል። የሽብር ቡድኑ የአገር ዳር ድንበር የሚጠብቀውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝን […]

የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያጸኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አይደለም፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14፣2013 የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያጸኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውስጥም ሆነ የውጭ ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ የትግራይ ህዝብ የመጀመሪያ ከለላ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በቦሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ደም በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። ዶክተር አብርሃም በላይ […]

ከ4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው 6 መቶ 38 ሳጥን ቢራን ከጫኑት ተሽከርካሪዎች ጋር ሰርቀው ሊሰወሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14፣2013  ከ4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው 6 መቶ 38 ሳጥን ቢራን ከጫኑት ተሽከርካሪዎች ጋር ሰርቀው ሊሰወሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን የፈፀሙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አዲሱ ሚካኤል ገነት ህንፃ ተብሎ በሚጠራው የቢጂ. አይ ኢትዮጵያ ምርቶች ወኪል አከፋፋይ አልታድ ኢትዮጵያ […]

ወርቅን በብር ቀይሮ ለማስቀመጥ በሚሰሩ አሻጥሮች አብዛኛው የወርቅ ምርት ባንክ እየገባ አደለም ተባለ።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣2013  ወርቅን በብር ቀይሮ ለማስቀመጥ በሚሰሩ አሻጥሮች አብዛኛው የወርቅ ምርት ባንክ እየገባ አደለም ተባለ። የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ይህንን ያሉት ከጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የማዕድን ዘርፉ በሚጠናከርበት ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው። ፈቃድ በተሰጣቸው የወርቅ አዘዋዋሪዎች አስፈላጊውን ክትትልና ጥናት በማካሄድ እርምጃ መውስድ እንሚያስፈልግም ነው የገለጹት። በጋምቤላ ክልል […]

የዲግሪ ተመራቂው ወጣት ቅድሚያ ለሀገር ህልውና ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገባ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013 በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ትምህርት በዲግሪ የተመረቀው ወጣት ስራ ቢያገኝም ቅድሚያ ለሀገር ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገባ፡፡ ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ወታደራዊ ስልጠናውን የተቀላቀለው ወጣት በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የትምህርት ዘርፍ የድግሪ ምሩቅ ሲሆን ስራ ቢያገኝም ቅድሚያ ለሀገሬ ህልውና ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገብቶ እየሰለጠነ ይገኛል፡፡ የዲግሪ ተመራቂው ነጋ ምህረት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ […]

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 1ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት ለመከተብ ዘመቻ ተጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013  በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 1ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ለመከተብ ዘመቻ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ አስታወቁ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኘውን የኮቪድ -19 ስርጭት በርብርብ መግታት ካልተቻለ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ዶክተር ዮሐንስ እንደገለጹት ባለፉት አራት ሳምንታት በኮቪድ -19 የመያዝ ምጣኔው፣ በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እና […]

በትግራይ ክልል ያለው ችግር የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው – የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013  በትግራይ ክልል ያለው ችግር የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ መንግሥታቸው ጣልቃ የመግባት አጀንዳን እንደማይደግፍ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡ በደበብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንትና የአገልግሎት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ከሆኑት ሁሴን አብዱል ባጊ አኮል ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ መክረዋል። አምባሳደር ነቢል የሁለቱ […]