loading
የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ስምምነት

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013  የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ እጩዎችን ለመምረጥ ተስማሙ ::የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ሞሮኮ ላይ ባደረጉት አዲስ ውይይት የእጩዎቹ የምልመላ ሂደት ከማክሰኞ ጀምሮ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ ተፋላሚ ሃይሎቹ የደረሱበት ስምምነት በሀገሪቱ ለአስር ዓመታት የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑ ነው የተመገረለት፡፡ ሂደቱ እስከመጭው ፌብሩዋሪ 2 ቀን ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን […]

በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ::

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013 በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ:: የሩሲያ የፀጥታ ሃይሎች ከ3 ሺህ በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ማሰራቸው ተሰማ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በቅርቡ ከህመም ያገገሙት የተቃዋሚ መሪው አሌክስ ናቫልኒ ከእስር ይፈቱልን የሚል ጥያቄ ይዘው ነው፡፡

በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡ የክትባቱ የውጤታማነት ደረጃ ሲለካ 89 ነጥብ 3 በመቶ እንደሆነ የእንግሊዝ የጤና ባለሙያዎች ይፋ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይህን መልካም ዜና እንደሰሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡ ኖቫቫክስ የተባለው ይህ ክትባት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመከላከል ውጤታማ ሆኖ የተገኘ […]

የማዕከላዊ አፍሪካ ዜጎች ወደጎረቤት ዲሞክራቲክ ኮንጎ መጠለያ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 የማዕከላዊ አፍሪካ ዜጎች ወደጎረቤት ዲሞክራቲክ ኮንጎ መጠለያ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡ ስደተኞቹ ቀያቸውን ጥለው የሚሰደዱት በሀገሪቱ ነፍጥ አንግበው ከሚዋጉ ሚሊሻዎች ጥቃት ህይዎታቸውን ለማዳን ሲሉ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት ከማዕከላዊ አፍሪካ ወደ ጎረቤትረ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የተሰደዱ 30 ሺህ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት […]

አይቤክስ ኮሌጅ ከፍለው መማር ለማይችሉ 150 ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 አይቤክስ ኮሌጅ ከፍለው መማር ለማይችሉ 150 ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ኮሌጁ ከተቋቋመ ከ2002 ጀምሮ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን ያስታወሱት የኮሌጁ ዲን አቶ ተስፍዬ አሰፋ ፤ እስካሁን ድረስ ከፍለው መማር ለማይችሉ 150 ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት ወደ ስራ ማስግባታቸውን ተናግረዋል። በዘንድሮው ዓመት በሆቴል ማኔጅመንት […]

ሞቃዲሾ ውስጥ የደረሰ የቦንብ አደጋ የሞትና የአካል ጉዳት አድርሷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 ሞቃዲሾ ውስጥ የደረሰ የቦንብ አደጋ የሞትና የአካል ጉዳት አድርሷል ተባለ:: አደጋው የተፈፀመው በማዕከላዊ ሞቃዲሾ በሚገኘው አፍሪክ ሆቴል ላይ ሲሆን ታጣቂዎች በአካባቢው ሁከት ከፈጠሩ በኋላ ፍንዳታው መከተሉን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ በአደጋው ሳቢያ አንድ ጡረተኛ የጦር ጄኔራልን ጨምሮ አምስት ሰዎች ህይዎታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ 10 ሰዎች በአደጋው ምክንያት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው አፍሪካ […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዳዲስ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዳዲስ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸው ተሰማ:: የቀድሞው ፕሬዚዳንት በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ህግ ተላልፈዋል መባላቸውን ተከትሎ ክስ ስለሚጠብቃቸው ራሳቸውን ለመከላkል ነው ይህን ያደረጉት ተብሏል፡፡ ትራምፕ ከሚጠብቃቸው ክስ ይከላከሉልኛል ያሏቸውን ዴቪድ ሾን እና ብሩስ ካስቶር የተባሉ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ትራምፕ አዳዲስ ጠበቆችን ለመቅጠር የተገደዱት የቀድሞዎቹ ጠበቆቻቸው ከሳቸው […]

ተጋነነ ዋጋ በሚያስከፍሉ ጫኝና አውራጆች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 27፣ 2013 ተጋነነ ዋጋ በሚያስከፍሉ ጫኝና አውራጆች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ፡፡ ዕቃ ለማውረድና ለመጫን የተጋነነ ዋጋን የሚጠይቁ ጫኝና አውራጆችን የማጣራት ሥራ በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ ለዕቃ ማውረድና መጫን የሚከፈለው ገንዘብ በዕቃ ባለቤትና በአውራጁ መካከል በሚደረገው […]

የአማዞን ቀጣይ ስራ አስፈጻሚ ይሆናል የተባለው ኤንዲ ጄሲ ማነው?

አዲስ አበባ፣ጥር 27፣ 2013 የአማዞን ቀጣይ ስራ አስፈጻሚ ይሆናል የተባለው ኤንዲ ጄሲ ማነው? ከዓለማችን ቁንጮ ቱጃሮች መካከል 2ኛው የሆነው ቤዞስ በግዙፉ የዓለማችን የበይነ መረብ ግብይት ተቋም አማዞን ያለውን ኃላፊነት ለሌላ ሰው እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡ ቤዞስ የአማዞን መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ነው፡፡ ትኩረቱን ወደ ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች የማዞር ውጥን እንዳለው ያስታወቀው ቤዞስ ዋና ስራ አስፈጻሚነቱን በመጪው […]

የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 28፣ 2013 የተፈናቀሉ ዜጎች በምርጫው የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉበት አሰራር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ”ይጠይቁ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የማህበራዊ ሚዲያ የተሳትፎ መድረክ ለቀረቡ ጥያቄዎች በቦርዱ የፌስቡክ ገጽ በቀጥታ ምላሽ ሰጥተዋል። […]