loading
በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ድሃና ወረዳ 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቋል። በምርቃቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰም ማሞና የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ የክልልና የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ […]

ጊኒ የኢቦላ ቫይረስ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች።

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 ጊኒ የኢቦላ ቫይረስ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች። በጊኒ ደቡብ ምስራቅ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች ባሻገር አራት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል። በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ጎዋኬ በአንድ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተሳተፉ 7 ሰዎች የማስመለስ፣ የመድማት እና ማስቀመጥ  እንዳጋጠማቸው ተጠቁሟል። የኢቦላ ቫይረስ የተገኘባቸው እነዚህ ሰዎች አሁን ላይ […]

የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባለፈው ሳምንት በ16 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባለፈው ሳምንት በ16 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገለፀ፡፡ ድርጅቱ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ባወጣው ሪፖርት ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዘ የሞት መጠን መቀነሱንም አስታውሷል፡፡ ድርጅቱ ከስድስት የቁጥጥር ቀጠናዎች ከተላኩለት የበሽታው ስርጭት ሪፖርቶች መካከል በአምስቱ አዲሱ ቫይረስ በሁለት አሃዝ መቀነስ ሲያሳይ በሜዲትራኒያን አካባቢ ብቻ በ7 በመቶ ጭማሪ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ […]

ኢዜማ መንግስት የፓረቲያቸዉን አባል ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፉት ባስቸኳይ እንዲያቀርብ ጠየቀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 ኢዜማ መንግስት የፓረቲያቸዉን አባል ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፉት ባስቸኳይ እንዲያቀርብ ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ የፓርቲዉ አባል አቶ ግርማ ግድያን ተከትሎ በሰጠዉ መግለጫ ፤ ከዚህ በፊት በቢሾፍቱ ከተማ የምናደርገዉ እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሙ እና አባላቶቻችን ላይ ማዋከብ ሲያገጥመን የቆየ ነዉ ብሏል፡፡ የምርጫ ወረዳ መዋቅራችን የሚጠቀምበት ጽ/ቤት ለመክፍት […]

አልጄሪያዊያን የሂራክ አመፅ ንቅናቄ ብለው የሚጠሩትን የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘከር አደባባይ ወጥተዋል፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 አልጄሪያዊያን የሂራክ አመፅ ንቅናቄ ብለው የሚጠሩትን የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘከር አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የሂራክ ንቅናቄ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2019 ፕሬዚዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካን ከስልጣን ያስወገዱበት የተቃውሞ ሰልፍ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ የኮሮናቫይረስ ሳያስፈራቸውና በአደባባይ በሰባሰብን የሚከለክለውን ህግ ወደጎን በመተው ነው እለቱን እያሰቡ ሌላ ጥያቄ ያነሱበት፡፡ አልጄሪያዊያኑ ያኔ ባነሱት ተቃውሞ ለሁለት አስርት ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ቡተፍላካ ከስልጣን […]

በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በላይ መድረሱ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በላይ መድረሱ ተነገረ፡፡ በአህጉሩ የተመዘገበው የሟችና የታማሚዎች ቁጥር ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር አናሳ ቢሆንም የበሽታው ስርጭት ከነበረበት በፍጥነት እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡ በተለይ በአፍሪካ ሁለተኛው ዙር የወረርሽኝ መስፋፋት መከሰቱን ተከትሎ ሆስፒታሎች በሽተኞችን መቀበል እስኪያቅታቸው መጨናነቃቸው ነው የሚነገረው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በአፍሪካ በሽታው ከታየ ጀምሮ እስካሁን ድረስ […]

የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ቲቦኒ የሀገሪቱን ፓርላማ በትነው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ቲቦኒ የሀገሪቱን ፓርላማ በትነው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አልጄሪያ የሰማእታት ቀንን በምታከብርበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ ቲቦኒ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት የተለያዩ የፓርቲ መሪዎች ጋር ተደጋጋሚ ስብሰባዎችና ምክክሮችን ካደረጉ በኋላ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሬዚዳንቱና የካቢኔ አባሎቻቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ […]

የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት 84ኛው የሠማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት 84ኛው የሠማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ:: በአድዋ ሽንፈትን የተከናነበው የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር የዛሬ 84 ዓመት ዳግም ኢትዮጵያን ሲወር በአራቱም አቅጣጫ ይፋለሙት በነበሩ ኢትዮጵያዊያ ላይ ግፍና በደል ፈጽሟል። ግፍና በደሉን አንቀበልም ያሉት አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ግራዚያኒን በቦምብ ለመግደል ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ተከትሎም የግራዚያኒ […]

ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡ ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ወ/ሮ አዳነች በየካቲት 12 ሆስፒታል በመገኘት ወረቀት አልባ ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓትን በይፋ ስራ አስጀምረዋል፡፡ በፕሮግራሙም ዛሬ የጀግኖች አርበኞች መታሰቢያ ቀን ለጀግኖች […]

በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ:: በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ። እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑ በወረርሽኝ ደረጃ ባይሆንም በጋምቤላ፣ አማራ፣ ሀረሪ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች፣ እንዲሁም በአዲስ […]