ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡ ኢንስቲትዩቱ በህንድ የተከሰተው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ መምጣቱን በማስታወስ ማህበረሰቡ እንዳይዘናጋ አስጠንቅቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ መግለጹን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሀገራት እንደተሰራጨ መገለጹን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡ […]