loading
የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባለ ስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የመከላከያ ምስክሮችን መስማት ጀመረ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013   የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባለ ስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የመከላከያ ምስክሮችን መስማት ጀመረ፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ እጃቸው አለበት በተባሉት በእነሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ የተከሰሱ 32 ተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች ነው ማዳመጥ የጀመረው፡፡ በዚሁ የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ ከነበሩት 55 ተከሳሾች […]

ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አባላት ላይ የዕድሜ ልክ እስራ  ውሳኔ አስተላለፈች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አባላት ላይ የዕድሜ ልክ እስራ  ውሳኔ አስተላለፈች፡፡ የሀገሪቱ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የፖሊስ አባላትን በመግደልና እስር ቤት ሰብረው እስረኞችን በማስመለጥ ወንጀል በተከሰሱ የህብረቱን መሪ ሞሐመድ ባዴን ጨምሮ በ10 ግለሰቦች ላይ ነው ወሳኔውን ያሳለፈው፡፡ ተከሳሾቹ እንደ አውሮፓያኑ አቆጣጠር በ2011 በግብፅ በተቀሰቀሰው አብዮት 20 ሺህ የሚሆኑ እስርኞችን እንዲያመልጡ […]

ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል-ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል-ጤና ሚኒስቴር በአዲስ አበባ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ባሉ የጤና ተቋማት ለኮሮና ቫይስ ተጋለጭ የሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎች እንዲከተቡ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ከወሰዱ ሶስት ወር የሞላቸው ዜጎች ከነገ ጀምሮ እንደሚከተቡ እና በክልሎች ደግሞ ክትባቱን ከሐምሌ 9 […]

በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡ በማገገሚያ ማዕከሉ በተቀሰቀሰው ቃጠሎ ከ64 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 70 የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ ፖሊስ የእሳት አደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም በሆስፒታሉ የሚገኝ ኦክስጂን መፈንዳት የአደጋው ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የገለጸው፡፡ አደጋውም […]

የአማራ ክልል በህወሓት ላይ የተጀመረው “ሕግን የማስከበር” ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7፣ 2013  የአማራ ክልል በህወሓት ላይ የተጀመረው “ሕግን የማስከበር” ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ:: በትግራይ ክልል በህወሓት ላይ የተጀመረው ሕግን የማስከበር ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሕዝብ አስፈላጊውን ርብርብ እንዲያደርግ የአማራ ክልል ጠየቀ፡፡ ክልሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ “ትህነግ አገር ከማፍረስ እኩይ ተልዕኮው ሊታቀብ የሚችለው የአገራችንን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት በጽናትና በአላማ ቁርጠኝነት በጋራ […]

የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጣር የወጣው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተነሳ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7፣ 2013  የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጣር የወጣው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱን አስታወቀ፡፡ በዚህ መሰረት የግብይት ሂደቱ በነፃ ገበያ መርህ እንዲከናወን ተወስኗል ብሏል። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት፥ በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ሲባል ወደ ቀደመ የነፃ ገበያ አሰራር ተመልሰናል […]

የቀጥታ በረራም ሆነ ከአውሮፕላን ላይ እርዳታ መጣል የሚለው ሀሳብ ተቀባይነት የላቸዉም::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ በቀጥታ በረራም ሆነ የሀገር ሉዓላዊነትን በሚጥስ ሌላ ተግባር የሚደረግ እንቅስቃሴ አይፈቀድም ተባለ:: የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና ሌሎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የእርዳታ አቅርቦቶች በተገቢው መንገድ ወደ መቀሌ እንዲያጓጓዙ […]

በትግራይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 በትግራይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ:: አሸባሪው ህወሓት ስደተኞች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ጥቃቶች መክፈቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባለከው መግለጫ እንደገለጸው፤ ህወሓት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ አድርጎ ስደተኞች ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው። በዚህ የህወሓት ጥቃት ምክንያት በማይ-ዓይኒ እና በአዲ-ሐሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች […]

የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ:: የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን ከትምህርት ቤት አግቶ በመውሰድ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ውጪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ የእገታ ወንጀሉ የተፈፀመው ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ […]

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተረከበች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 አሜሪካ ለኢትዮጵያ የለገሰችውን 453 ሺህ 600 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ጤና ሚኒስቴር ተረከበ:: በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የተደረገው ድጋፍ  ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው  ክትባት ሲሆን ቃል ከገባችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ 453 ሺህ 600 ዶዙ አዲስ አበባ  ገብቷል። ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት […]