loading
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራ እና አፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን ላጠና ነው አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት ጦርነት በነበረባቸው የአማራና አፋር ክልሎችና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሰውን የሕይወትና የንብረት ውድመት በመስክ የሚያጠና ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የጥናትና የምርምር ስራውን ጀምሯል። ከጥናትና ምርምር ቡድኑ የሚደርስበት ግኝት ውድመቱን ያደረሰውን አሸባሪ ቡድን የታሪክ ተወቃሽ በማድረግ በቀጣይ ለሚኖሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይውላል ብለዋል። […]

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ “ዳያስፖራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርእስ የዳያስፖራ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የዳያስፖራ አባላቱ አሸባሪው ህወሃት በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ያደረሰውን ጉዳትና ውድመት ለመጎብኘት ነው ትናንት አመሻሽ ወደ ስፍራው ያቀኑት፡፡ የዳያስፖራ አባላቱ ሰመራ ከተማ ሲገቡ በክልሉ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በዛሬው ዕለት የምክክር መድረክ ጀምረዋል። አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል በትምህርት፣ በጤና እና በግብርና ዘርፎች ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል […]

የላልይበላ በረራ ዳግም መጀመር ቱሪዝምን ለማነቃቃት ዘርፉ ያለው ሚና…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የላልይበላ በረራ ዳግም መጀመሩ ተሰማ፡፡ አየር መንገዱ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ተከትሎ ነበር በረራውን ያቋረጠው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን የልደት በዓልን በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልበይላ ለሚያከብሩ ምዕምናንና አካባቢውን ለሚጎበኙ ተጓዦች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ዘረፋና ውድመት የደረሰበትን […]