loading
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራ እና አፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን ላጠና ነው አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት ጦርነት በነበረባቸው የአማራና አፋር ክልሎችና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሰውን የሕይወትና የንብረት ውድመት በመስክ የሚያጠና ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የጥናትና የምርምር ስራውን ጀምሯል። ከጥናትና ምርምር ቡድኑ የሚደርስበት ግኝት ውድመቱን ያደረሰውን አሸባሪ ቡድን የታሪክ ተወቃሽ በማድረግ በቀጣይ ለሚኖሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይውላል ብለዋል። […]

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ “ዳያስፖራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርእስ የዳያስፖራ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የዳያስፖራ አባላቱ አሸባሪው ህወሃት በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ያደረሰውን ጉዳትና ውድመት ለመጎብኘት ነው ትናንት አመሻሽ ወደ ስፍራው ያቀኑት፡፡ የዳያስፖራ አባላቱ ሰመራ ከተማ ሲገቡ በክልሉ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በዛሬው ዕለት የምክክር መድረክ ጀምረዋል። አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል በትምህርት፣ በጤና እና በግብርና ዘርፎች ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል […]

የላልይበላ በረራ ዳግም መጀመር ቱሪዝምን ለማነቃቃት ዘርፉ ያለው ሚና…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የላልይበላ በረራ ዳግም መጀመሩ ተሰማ፡፡ አየር መንገዱ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ተከትሎ ነበር በረራውን ያቋረጠው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን የልደት በዓልን በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልበይላ ለሚያከብሩ ምዕምናንና አካባቢውን ለሚጎበኙ ተጓዦች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ዘረፋና ውድመት የደረሰበትን […]

ምዕመናን የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ ጥሪ መቅረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 በልበ ሙሉነት የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ ጥሪውን ያስተላለፉት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናትና ገዳማት አስተዳዳሪ አባ ፅጌ ሥላሴ መዝገቡ ናቸው፡፡ አካባቢው በችግር ውስጥ እንደነበር ያስታወሱት አባ ፅጌ ሥላሴ ሁላችንም በከባድ ሐዘን ውስጥ ነበርን፤ አሁን ግን ከወገናችን ጋር በዓሉን በተለመደው መልኩ ለማክበር ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ የተለመደው አገልግሎት ሳይጓደል […]

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ:: ግዥው የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ከማስፍን አንጻር የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ፋይዳ እንዳለው የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን የገለጸው የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀናት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ባለፉት ጥቅምትና ህዳር ወራት የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ […]

የሠራዊቱን ስም ማጠልሸት በሀገር ላይ አደጋ ለመጣል መሞከር ነው-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሠራዊቱ ላይ አሉባልታ የሚነዙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቁ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአገር መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የጸጥታ አከላት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ ተደቅኖ የነበረውን የህልውና አደጋ በመቀልበስ አኩሪ ገድል መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡ ሠራዊቱ የሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አብራክ ክፋይና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የመጨረሻው […]

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት ከቤቶች ግንባታ ጋር በተያያዘ የ54 ቢሊዮን ብር እዳ የመክፈል ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት ከቤቶች ግንባታ ጋር በተያያዘ የ54 ቢሊዮን ብር እዳ የመክፈል ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ፡፡ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በስምንት ቢሊዮን ብር በጀት የአምስት ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።ይህ የተጀመረው የቤቶች ፕሮጀክት በተገጣጣሚ ቴክኖሎጂ የሚሰራና በአጭር ጊዜ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ነው ተብሏል። ከንቲባዋ በፕሮግራሙ […]

በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ቃጠሎ ተጠርጥሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሰው የጎዳና ተዳዳሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 ከደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረው ግለሰብ ሽብርተኝነትን ጨምሮ ከ6 በላይ ክስ ተመሰረተበት፡፡ ትናንትና ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት የቀረበው የ49 ዓመቱ የጎዳና ተዳዳሪ ዜንዳይል ክሪስርማስ ማፊ ከሽብርተኝነት በተጨማሪ በዘረፋና ከባድ የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት ወንጀሎች መከሰሱም ተሰምቷል፡፡ የአቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ኤሪክ ንታባዛሊላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ […]

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት በዲፕሎማሲው አውድ መሻሻሎችየመኖራቸው ማሳያ ነው ሲል -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ከዚህ ቀደም የነበረውን የግንኙነት መንፈስ እየተቀየረ ለመሆኑ ማሳያ […]

በሞቃዲሾ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 በሞቃዲሾ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በአደጋው ከሞቱት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም ተነግሯል፡፡ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ቡድን ጥቃቱን ስለማድረሱ ሃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን ጥቃቱምለጉዞ በአየር መንገዱ የተገኙ ነጭ ባለስልጣናትን ዒላማ ያደረገ ነበር ብሏል፡፡ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ፍንዳታው በተከሰተበት […]