loading
አሜሪካ የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈጸሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ስትል ገለጸች፡፡

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 አሜሪካ የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈጸሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ስትል ገለጸች፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአመንስቲ አንተርናሽናልን ሪፖርትን መነሻ አድርጎ ባወጣው መግለጫ በክልሉ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የተፈጸሙ በርካታ ወንጀሎች አሳሳቢ ናቸው ብሏል፡፡መግለጫው አክሎም በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ ግፍና ወንጀል በሚገባ ተጣርቶ የድርጊቱፈጸሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥር አቅርቧል፡፡ የትኛውም የታጠቀ […]

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባበለጸጋቸው ስርዓቶች ውስጥ የሚተገበሩ ከ200 በላይ አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆኑን ገለጸ።

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባበለጸጋቸው ስርዓቶች ውስጥ የሚተገበሩ ከ200 በላይ አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆኑን ገለጸ። ተጨማሪ 45 የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስችሉ ስርዓቶች ለምተው መመረቃቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡ሚኒስቴሩ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጋር አገልግሎቶቹ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲተገበሩ ለማድረግ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራሟል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ የመንግስት አገልግሎቶችን […]

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራሁ ነው አለ፡፡

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራሁ ነው አለ፡፡ ኩባንያው ይህን የገለጸው በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስገነባቸውን መሰረተ ልማቶችና የዳታ ቤዝ ማእከሉን ለጋዜጠኞች ባስጎበኘበት ወቅት ነው፡፡ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራ መሆኑን የኩባንያው የውጭ ጉዳይና የቁጥጥር ኦፊሰር ማቴ ሃሪሰን ሃርቬይ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ማሸነፉን […]

ዩጋንዳ የኮቪድ-19 መከላከያ ያልተከተቡ ሰዎችን በገንዘብና በእስራት መቅጣት የሚያስችል ህግ አረቀቀች::

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 ዩጋንዳ የኮቪድ-19 መከላከያ ያልተከተቡ ሰዎችን በገንዘብና በእስራት መቅጣት የሚያስችል ህግ አረቀቀች፡፡ ለሀገሪቱ ፓርላማ የቀረበው ይህ የህግ ረቂቅ ክትባት ለመውሰድ አሻፈረኝ በሚሉ ዜጎች ላይ 1 ሺህ 139 ዶላር ወይም 4 ሚሊዮን የሀገሪቱን ገንዘብ የሚያስቀጣ ሲሆን የሥድስት ወር እስራትንም ያካትታል፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ጄን ሩት አሴንግ ረቂቅ ህጉን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ዜጎችን […]