loading
በሶማሊያ በተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶች የ48 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 በሶማሊያ በተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶች የ48 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ በማዕከላዊ ሶማሊያ በተፈፀሙት ጥቃቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 48 ከፍ ያለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የሂርሻቤል ግዛት አስተዳዳሪ የአልሸባብ አማፂያን ከምርጫው በፊት ፖለቲከኞች ላይ ማነጣጠራቸውንአስታውቀዋል። መጀመርያ በሂርሻቤል ቤልደዌን አውራጃ በተፈፀመው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት አሚና መሀመድ አብዲን ጨምሮ ሁለት የአካባቢው ህግ አውጪዎች […]

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ‘ካፒቶል ሂል’ ፊት ለፊት በሚካሄደው ሰልፍ ረቂቅ ሕጎቹ የኢትዮጵያን ሕልውና የሚጎዱ በመሆኑ ውድቅ መሆን አለበት የሚሉ መልዕክቶች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡ ሕጎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየውን በኢትዮጵያና አሜሪካ […]

ኢምፔሬያሊስቶችን አደብ ማስገዛት የሚቻለው ወታደራዊ አቅምን ባማሳደግ ነው-ኪም ጆንግ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 ኢምፔሬያሊስቶችን አደብ ማስገዛት የሚቻለው ወታደራዊ አቅምን ባማሳደግ ነው-ኪም ጆንግ ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡን ሀገራቸው የሚሳኤል ጦር መሳሪያ ትጥቋን ይበልጥ ለማዘመን ማቀዷን ይፋ አደረጉ፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ 12 የሚሳኤል ሙከራዎችን ያደረገችው ፒዮንግያንግ ሰሞኑን አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯ በአሜሪካና አጋሮቿ ዘንድ ስጋትና ቁጣን ቀስቅሷል ነው የተባለው፡፡ ዋሶንግ […]

ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን ከራስ ወዳድነት የሚያርቁበት ወር ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 ታላቁ የረመዳን ወር ይቅር የምንባባልበት መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ገልጸዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲው ይህን ያሉት የታላቁ ረመዳንን ወር ፆም አስመልክቶ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ በመግለጫቸውም ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ የሚያርቁበት ወር ብቻ ሳይሆን መልካም በመስራት ራሳቸውን ከፈጣሪያቸው ጋር ይበልጥ የሚያቀራርቡበት ነው […]

የሱዳን የሽግግር መንግስት መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ በካይሮ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 የሱዳን የሽግግር መንግስት መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ በካይሮ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡አልቡራሃን ወደ ካይሮ በመጓዝ ከፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራትመካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በደህንነትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ውይይትአድርገዋል፡፡በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ የተቀመጡት ጄኔራል አልቡራሃን በሀገራቸው የተፈጠረውንአለመረጋጋት መልክ ለማስያዝ የግብፅን ድጋፍ ጠይቀዋል ነው የተባለው፡፡ፕሬዚዳንት አልሲሲ በበኩላቸው ግብፅና ሱዳን […]